በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዓለም ጤና ድርጅት አንድ ሰራተኛው በሶማሊያ ሆቴል ጥቃት መገደሉን አስታወቀ


ፋይል - ሞቃዲሾ በሚገኘው ፐርል ቢች ሆቴል ላይ ጥቃት በተፈፀመበት ቦታ ነዋሪዎች ቆመው የደረሰውን ጉዳት ሲመለከቱ - ሰኔ 10፣ 2023
ፋይል - ሞቃዲሾ በሚገኘው ፐርል ቢች ሆቴል ላይ ጥቃት በተፈፀመበት ቦታ ነዋሪዎች ቆመው የደረሰውን ጉዳት ሲመለከቱ - ሰኔ 10፣ 2023

በሶማሊያ ዋና ከተማ ሞቃዲሾ ውስጥ፣ በባህር ዳርቻ ላይ በሚገኝ ሆቴል በሳምንቱ መጨረሻ ላይ በተፈፀመው ጥቃት ከተገደሉት መካከል የዓለም ጤና ድርጅት ሰራተኛ እንደሚኝበት፣ የጤና ድርጅቱ ሀላፊ እሁድ እለት አስታወቁ።

በጥቃቱ ስድስት ንፁሃን ዜጎች ሲገደሉ ሌሎች አስር ሰዎች ደግሞ መቁሰላቸውን ፖሊስ አስታውቋል።

የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ቴድሮስ አድሃኖም በትዊተር ገፃቸው ላይ ባሰፈሩት መልዕክት "በቅርቡ በሶማሊያ፣ ሞቃዲሾ በተፈፀመው ጥቃት አንድ የዓለም ጤና ድርጅት ሰራተኛ በማጣታችን ልቤ ተሰብሯል" ያሉ ሲሆን ለቤተሰቦቻቸው እና ዘመዶቻቸውን በሞት ላጡ ሁሉ መፅናናትን ተመኝተዋል።

"በሲቪሎች እና በሰብዓዊ ሰራተኞች ላይ የሚደርሰውን ጥቃት ሁሉ እናወግዛለን" በማለትም ሀዘናቸውን ገልፀዋል።

አል-ሻባብ ሀላፊነቱን የወሰደበት ይህ ጥቃት የጀመረው አርብ እለት ከምሽቱ 2-ሰዓት አካባቢ ሲሆን፣ ሰባት ጥቃት አድራሽ ታጣቂዎች በሞቃዲሾ ባህር ዳርቻ ላይ የሚገኘውን ፐርል ቢች ሆቴል በመውረር እስከ ለሊቱ ስምንት ሰዓት ድረስ ከፀጥታ ሀይሎች ጋር ተዋግተዋል። በተኩስ ልውውጡ ወቅት ሁሉም ታጣቂዎች መገደላቸውን ፖሊስ አስታውቋል።

XS
SM
MD
LG