በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

መንግሥት አልሸባብ በሞቃድሾ ሆቴል ያደረሰው ጥቃት አብቅቷል አለ



በታጣቂው ቡድን፣ አልሸባብ ጉዳት የደረሰበት የፐርል ቢች ሆቴል ሞቃዲሾ፣ ሶማሊያ፣ እኤአ ሰኔ 10፣ 2023 ዓም
በታጣቂው ቡድን፣ አልሸባብ ጉዳት የደረሰበት የፐርል ቢች ሆቴል ሞቃዲሾ፣ ሶማሊያ፣ እኤአ ሰኔ 10፣ 2023 ዓም

የሶማልያ መንግሥት ትናንት ዓርብ ሞቃድሾ በሚገኘው ሆቴል ላይ በአልሻባብ ታጣቂዎች የተጀመረው ጥቃት ማብቃቱን አስታወቀ፡፡

የደህንነት ኃይሎች ፐርል ቢች በተባለው ሆቴል ላይ የተካሄደውን ጥቃት ትንናት ምሽቱን በተሳካ ሁኔታ መቆጣጠራቸውን መንግሥት ገልጿል፡፡

በርካታ ቁጥር ያላቸው ሲቪሎች በደህንነት ኃይሎች መታደጋቸውንም የመንግሥት መገናኛ ብዙሃን ዘግቧል፡፡

የሶማልያ ፖሊስ በጥቃቱ ዘጠኝ ሰዎች መገደላቸውና 10 የሚደርሱት ደግሞ መቁሰላቸውን አስታውቋል፡፡

ከተገደሉት መካከል ስድስቱ ሰላማዊ ዜጎች ሲሆኑ ሶስቱ ደግሞ የጸጥታ ኃይሎች መሆናቸውን የሶማልያ ፖሊስ ባወጣው መግለጫ አመልክቷል፡፡

ህጻናት ሴቶችና አረጋውያንን ጨምሮ 84 የሚደርሱ ሰዎችን ጥቃቱ ከደረሰበት ስፍራ መታደግ መቻሉን ፖሊስ ጨምሮ አስታውቋል፡፡

የዐይን ምስክሮች ለአሜሪካ ድምጽ የሶማልኛው አገልግሎት እንደተናገሩት፣ ጥቃቱ የተጀመረው ከሆቴሉ ውጭ በደረሱ ቢያንስ ሁለት ፍንዳታዎች እና እሱንም ተከትሎ ወደ ሆቴሉ በዘለቁ ታጣቂዎች አማካይነት ነው፡፡

የተኩስ ድምጽ እንደተሰማም ህንጻው ውስጥ የነበሩ በርካታ ሰዎች መውጫ ማጣታቸውንና ሌሎችም በጓሮ በሮችና መስኮት በኩል ማምለጣቸውን ምስክሮቹ ተናግረዋል፡፡

ልዩ የደህንነት ኃይሎች ወደ ህንጻው ዘልቀው የገቡት ከላይ በሆቴሉ ጣራ በኩል መሆኑንም የዐይን እማኞቹ ለቪኦኤ አክለው ገልጸዋል፡፡

ከአልቃይዳ ጋር ግንኙነት እንዳለው የሚነገረው አልሸባብ ለጥቃቱ ኃላፊነቱን ወስዷል፡፡

XS
SM
MD
LG