በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሕግ ማስከበር ስም ወደ ዐማራ ክልል የገባው የሀገር መከላከያ ሠራዊት እንዲመለስ ተጠየቀ


በሕግ ማስከበር ስም ወደ ዐማራ ክልል የገባው የሀገር መከላከያ ሠራዊት እንዲመለስ ተጠየቀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:07 0:00

የፌዴራል መንግሥት፣ በሕግ ማስከበር ስም ወደ ዐማራ ክልል ያስገባውን፣ የሀገር መከላከያ ሠራዊት ከክልሉ እንዲያስወጣ፣ በዐማራ ክልል ምክር ቤት የዐማራ ብሔራዊ ንቅናቄ /አብን/ ተመራጭ የሕዝብ እንደራሴዎች ጠየቁ፡፡

በቁጥር 13 የኾኑ፣ የአብን ተወካይ የምክር ቤቱ አባላት፣ ዛሬ ባወጡት መግለጫ፣ “የፌዴራል መንግሥቱ፥ በዐማራ ላይ ከሕግ እና አሠራር ውጪ ጦርነት ከፍቷል፤” ብለዋል። የክልሉ ምክር ቤትም፣ በጉዳይ ላይ እንዲወያይ ጠይቀዋል።

ከምክር ቤቱ አባላት መካከል፣ ለአሜሪካ ድምፅ አስተያየት የሰጡ አንድ የምክር ቤቱ አባል፣ የፌዴራል መንግሥቱ፥ በዐማራ ክልል ታጥቀው የሚንቀሳቀሱ ኃይሎች አሉ ብሎ ካመነ፣ በሌሎች ክልሎች እንዳደረገው፣ ችግሮችን በድርድር መፍታት እንደሚኖርበት አመልክተዋል፡፡

በዚኹ ጉዳይ ላይ፣ ከክልሉ መንግሥት ምላሽ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት ሊሳካልን አልቻለም፡፡ ኾኖም የፌደራል መንግሥቱ፣ መጋቢት 20 ቀን 2015 ዓ.ም. በጸጥታ እና ደኅንነት ግብረ ኃይሉ በኩል ባወጣው መግለጫ፣ በዐማራ ክልል፣ ሕገ መንግሥታዊ ሥርዐቱን ለማፍረስና ክልላዊ ሥልጣኑን በኃይል ለመቆጣጠር በሚጥሩ ጽንፈኛ ብሎ በጠራቸው ኃይሎች ላይ ርምጃ መውሰድ መጀመሩን ማስታወቁ ይታወሳል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

XS
SM
MD
LG