በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በደቡብ እና በሲዳማ ክልሎች ሰባት ሚሊዮን ሕዝብ ለኮሌራ ወረርሽኝ ተጋልጧል


በደቡብ እና በሲዳማ ክልሎች ሰባት ሚሊዮን ሕዝብ ለኮሌራ ወረርሽኝ ተጋልጧል
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:03 0:00

በደቡብ እና በሲዳማ ክልሎች ሰባት ሚሊዮን ሕዝብ ለኮሌራ ወረርሽኝ ተጋልጧል

በደቡብ ክልል እየተዛመተ ባለው የኮሌራ ወረርሽኝ፣ በደቡብ ኦሞ ዞን፣ 234 ሰዎች በበሽታው መያዛቸውን፣ የዞኑ ጤና መምሪያ አስታውቋል፡፡

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብአዊ ጉዳዮች ማስተባበርያ ቢሮ(UN-OCHA) በበኩሉ፣ ወረርሽኙ፣ በክልሉ፥ በአርባ ምንጭ እና በዲላ ከተሞች፣ እንዲሁም በሲዳማ ክልል ሐዋሳ ከተማ መዛመቱን ጠቅሶ፣ በአጠቃላይ ሰባት ሚሊዮን ሰዎች ተጋላጭ እንደኾኑ፣ በሰሞኑ ሪፖርቱ አስታውቋል።

የኮሌራ ወረርሽኝ የጤና ስጋት እንዳይኾን፥ ንጹሕ የመጠጥ ውኃ ማቅረብ፣ የጤና መሠረት ልማትን ማሟላት፣ እንዲሁም ስለ ግል እና የአካባቢ ንጽሕና ለኅብረተሰቡ አስተማማኝ ግንዛቤ ማስያዝ እንደሚያስፈልግ፣ የአሜሪካ ድምፅ ያነጋገራቸው፣ በሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስፔሻል ሪፌራል ሆስፒታል የከፍተኛ ክሊኒክ አገልግሎት ዲሬክተር ዶክተር ክብሩ ክፍሌ አስረድተዋል።

XS
SM
MD
LG