በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በአልሸባብ ጥቃት  54 ሰላም አስከባሪ ወታደሮቿ መገደላቸውን ዩጋንዳ አስታወቀች። 


 የዩጋንዳ ሰላም አስከባሪ ወታደሮች በሶማሊያ ሞቃዲሾ አውሮፕላን ማረፊያ በተካሄደ ሥነ ሥርዓት ላይ
የዩጋንዳ ሰላም አስከባሪ ወታደሮች በሶማሊያ ሞቃዲሾ አውሮፕላን ማረፊያ በተካሄደ ሥነ ሥርዓት ላይ

ባለፈው ሳምንት በሶማሊያ የሚገኘውን የአፍሪካ ህብረት ጦር ሰፈር ታጣቂዎች ከበው በወሰዱት እርምጃ 54 የዩጋንዳ ሰላም አስከባሪ ኃይል አባላት መገደላቸውን ፕሬዚደንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ ተናገሩ። ጥቃቱ በጦርነቱ በደቀቀችው ሀገር ውስጥ በአልሸባብ ጅሃዳዊያን ከደረሱት አስከፊ ጥቃቶች አንዱ መሆኑም ተገልጿል ።

ሙሴቬኒ ቅዳሜ መገባደጃ ላይ በትዊተር ገፃቸው "አንድ የጦር አዛዥን ጨምሮ የ54 ወታደሮች በድን አግኝተናል " ብለዋል።

አንጋፋው መሪ ሀገሪቱን ከሚያስተዳድረው ብሄራዊ ተጋድሎ ንቅናቄ ፓርቲያቸው አባላት ጋር መነጋገራቸውን ጽ/ቤታቸው ለአጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ገልጿል ።በአፍሪካ ህብረት ኃይል የሚታገዘው ማዕከላዊ መንግስት ደጋፊ ኃይሎች በአልሸባብ ላይ ባለፈው ነሃሴ ወር ጥቃት ከከፈቱ ወዲህ የአሁኑ ጉዳት እጅግ ከባድ መሆኑ ተነግሯል ።

የሙሴቬኒ ንግግር በአፍሪካ ኅብረት አባላት ዘንድ ያልተለመደ ጉዳትን የማመን እርምጃም መሆኑ ተጠቅሷል። በሶማሊያ ደካማ በሆነው ማዕከላዊ መንግስት ላይ ከአስር አመታት በላይ አስከፊ ሽምቅ ውጊያ ሲያካሂድ የቆየው አልሸባብ በአውሮጳዊያኑ ግንቦት 26 በዩጋንዳ ሰላም አስከባሪዎች ጦር ሰፈር ላይ ጥቃት ከፍቶ 137 ወታደሮችን መግደሉን ተናግሯል።

አልሸባብ በጦር ሜዳ አገኘሁት የሚለውን ድል ለፕሮፓጋንዳ ፍጆታ ሲል በማጋነን ስለሚታወቅ ፣ ለአፍሪካ ኅብረት ጦር ሠራዊት የሚያዋጡ መንግሥታትም ለደረሰው ጉዳት ማረጋገጫ የሚሰጡት አልፎ አልፎ ብቻ ነው።

የአልሸባብ ታጣቂዎች ከዋና ከተማይቱ ሞቃዲሾ በስተደቡብ ምዕራብ 120 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ቡሎ ማሬር የሚገኘው የጦር ሰፈር ፈንጂ በጫነ መኪና ጥሰው ከገቡ በኃላ ውጊያ መደረጉን የአካባቢው ነዋሪዎች እና የሶማሊያ ወታደራዊ አዛዥ ለኤጀንሲ ተናግረዋል።

XS
SM
MD
LG