በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በታጣቂዎች በታጎለው የምዕራብ ኢትዮጵያ የመጓጓዣ አገልግሎት ነዋሪዎች ለእንግልት እንደተጋለጡ ተናገሩ


በታጣቂዎች በታጎለው የምዕራብ ኢትዮጵያ የመጓጓዣ አገልግሎት ነዋሪዎች ለእንግልት እንደተጋለጡ ተናገሩ
please wait

No media source currently available

0:00 0:09:51 0:00

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ካማሺ እና በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ዞኖች መካከል፣ የመጓጓዣ አገልግሎት ከተቋረጠ ከሦስት ወራት በላይ ማስቆጠሩን፣ የአሜሪካ ድምፅ ያነጋገራቸው ነዋሪዎች እና ነጋዴዎች ገለጹ።

አስተያየት ሰጪዎቹ፣ የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊትን ማስፈራሪያ እና ዝርፊያ በመስጋት አገልግሎቱ መቋረጡን ሲገልጹ፣ ይህም፣ ኅብረተሰቡን ለእንግልት ማጋለጡንና የፍጆታ እቃዎችን ወደ አካባቢው ለማስገባት አስቸጋሪ ኹኔታ በመፍጠሩ የዋጋ ንረትን ማስከተሉን፣ አክለው ተናግረዋል።

የዞኑ ኮምዩኬሽን መምሪያ በበኩሉ፣ አገልግሎቱ እንዲቋረጥ መንሥኤ የኾነው፣ በአካባቢው የሚደረገው የታጣቂዎች እንቅስቃሴ ስለመኾኑ፣ ከነጋዴዎች ማረጋገጡን አስታውቋል።

የምዕራብ ወለጋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሰሎሞን ታምሩ በበኩላቸው፣ “ሸኔ” ብለው የጠሩትና በአካባቢው የሚንቀሳቀሰው የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት፣ የዝርፊያ ተግባር በመፈጸሙ፣ ባለሀብቶች በመንገዱ ላይ መንቀሳቀስ በመስጋታቸው፣ የመጓጓዣ አገልግሎቱ መቋረጡን ገልጸው፣ የመንግሥት ኃይሎች ወደ አካባቢው እንደሚሠማሩ አስታውቀዋል።

በተጨማሪም፣ የኦሮሚያ፣ ቤኒሻንጉል ጉምዝ እና ጋምቤላ ክልሎች፣ የጋራ ሰላም እና ልማት ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት፥ ከሚመለከታቸው የምዕራብ ወለጋ እና የቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል አመራሮች ጋራ ችግሩን ለመቅረፍ እየሠሩ ስለመኾኑ ገልጿል።

በሌላ በኩል፣ የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት ዓለም አቀፍ ቃል አቀባይ ኦዳ ተርቢ፣ በአካባቢው፥ ታጣቂዎቻቸው ከመንግሥት ጋራ ውጊያ እያካሔደ በመኾኑ፣ የኅብረተሰቡ እንቅስቃሴ መገታቱን ጠቅሰው፣ የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት ግን በአካባቢው ዝርፊያ አልፈጸመም፤ አይፈጽምም፤” ሲሉ አስተባብለዋል።

XS
SM
MD
LG