በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አክራሪው የእስራኤል የካቢኔ ሚኒስትር የእየሩሳሌም ቅዱስ ቦታን ጎበኙ


አክራሪው የእስራኤል የካቢኔ ሚኒስትር አወዛጋቢውን የእየሩሳሌም ቅዱስ ቦታን ጎበኙ
አክራሪው የእስራኤል የካቢኔ ሚኒስትር አወዛጋቢውን የእየሩሳሌም ቅዱስ ቦታን ጎበኙ

ከፍልስጤማውያን ጋር ከፍተኛ ውጥረት በነገሰበት በአሁኑ ወቅት አንድ አክራሪ የእስራኤል የካቢኔ ሚኒስትር እሁድ እለት አወዛጋቢ የሆነውን የኢየሩሳሌም ቅዱስ ስፍራን ጎብኝተዋል።

የእስራኤል ቀኝ ዘመም መንግስት አባል ከሆኑ ወዲህ ለሁለተኛ ጊዜ ወደዚያው ያቀኑት የብሄራዊ ደህንነት ሚኒስትሩ ኢታማር ቤን-ጊቪር ጉብኝት የስፍራው የአደራ ጠባቂ ሆና ከምትሰራው ፣ የፍልስጤማውያን እና የእስራኤል ጎረቤት ዮርዳኖስ ውግዘት አስከትሏል።

"ለእስራኤላውያን በእጅግ አስፈላጊው ወደሆነው ቤተ መቅደስ ተራራ በመምጣቴ ደስተኛ ነኝ" ብለዋል ቤን-ጂቪር ጠዋት ላይ ስፍራውን በጎበኙበት ወቅት ። በቢሯቸው በኩል በተለቀቀ ቪዲዮ ላይ በቦታው ላይ ፖሊስ መገኘቱንም አድነቀዋል ፣ ይህም “በኢየሩሳሌም ውስጥ (ወሳኝ) ማን እንደሆነ ያሳያል” ሲል አሞካሽተዋል።

የፍልስጤም ፕሬዚዳንታዊ ቃል አቀባይ ናቢል አቡ ሩዲኔህ የቤን-ጊቪርን ጉብኝት በመስጊዱ ላይ “ ዐይን ያወጣ ጥቃት” ሲሉ ጠርተውታል። የዮርዳኖስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር “የተወገዘ ጠብ ቀስቃሽ ፣ አደገኛ እና ተቀባይነት የሌለው ሁኔዎችን የሚያባብስ እርምጃ ” ሲሉ ኮንነውታል ።

ዘገባው የአሶሼትድ ፕረስ ነው ።

XS
SM
MD
LG