በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በቡርኪና ፋሶ በጂሃዲስቶች የሚፈጸመው ግድያ ቀጥሏል


ፎቶ ፋይል (ኤኤፍፒ)
ፎቶ ፋይል (ኤኤፍፒ)

በቡርኪና ፋሶ በጂሃዲስቶች ይፍጸማል የሚባለው ግድያ እንደቀጥለ ነው። ዛሬ 12 ሰዎች በምዕራብ የአገሪቱ ክፍል እንደተገደሉ የኤኤፍ ፒ ዘገባ አመልክቷል።

ባለፈው ሐሙስ 20 የሚሆኑ ሰዎች በአገሪቱ ሰሜን ሲገደሉ፣ ትናንት ዓርብ ደግሞ ሌሎች 20 ሰዎች በአገሪቱ ምሥራቅ መገደላቸው ተዘግቧል። ባለፈው ሰኞ እንዲሁ ታጣቃዎች በአገሪቱ ደቡብ ምሥራቅ የሚገኝ መንደር ውስጥ ገብተው ሴቶችን እና ህጻናትን ጨምሮ 11 ሰዎችን ገድለዋል።

በያዝነው ሳምንት ብቻ ከ40 በላይ ሰዎች ተገድለዋል።

ከማሊ የሚመጡ ናቸው በሚባሉ የእስልምና ነውጠኞች ላለፉት ስምንት ዓመታት ተፈጽሟል በተባለ ጥቃት፣ በቡርኪና ፋሶ ከ 10 ሺህ በላይ ሰዎች መገደላቸው ሲነገር፣ ቢያንስ 2 ሚሊዮን የሚሆኑት ተፈናቅለዋል። አንድ ሶስትኛ የሚሆነው የአገሪቱ ክፍል ከመንግስት ቁጥጥር ውጪ ነውም ተብሏል።

XS
SM
MD
LG