በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የቡድን 7 መሪዎች ቻይናን አወገዙ


ፎቶ ኤፒ (ግንቦት 20፣ 2023)
ፎቶ ኤፒ (ግንቦት 20፣ 2023)

በእንዱስትሪ የበለጸጉት የቡድን 7 አገራት መሪዎች ሂሮሺማ፣ ጃፓን ላይ በጀመሩት ጉባኤ፣ ቻይና በኢኮኖሚም ሆነ በወታደራዊ መስክ በዓለም ላይ የደቀነችውን ስጋት አውግዘዋል። አገራቱ ባወጡት የጋራ መግለጫ ሩሲያ በዩክሬን ላይ የምታካሂደውን ጦርነት እንድታቆም እና ሠራዊቷን እንድታስወጣ ቻይና ያላትን ተጽእኖ እንድትጠቀም ጥሪ አድርገዋል። የቡድን 7 አገራቱ በሩሲያ የተፈጸመውን ሕገ ወጥ ያሉትን ወረራ ለመመከትና ለዩክሬን ያላቸውን ድጋፍም ገልጸዋል።

የዩክሬኑ ፕሬዝደንት ቮሎዲሚር ዜሌንስኪ በቡድን 7 ጉባኤ ላይ ተገኝተዋል።

ሩስያ በአገራቸው ላይ ጦርነት ከከፈተች ወዲህ ያደረጉት ረጅሙ የውጪ ጉዞ ነው ተብሏል።

ዜሌንስኪ በሂሮሺማ ከእንግሊዙ ጠቅላይ ሚኒስትር ሪሺ ሱናክ እንዲሁም፣ ከጣሊያኗ ጠቅላይ ሚኒስትር ጂዮርጂያ ሜሎኒ ጋር ተገናኝተው ተነጋግረዋል።

ከህንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ጋር ባደረጉት ስብሰባ፣ ናሬንዳራ ሞዲ ለዩክሬን ያላቸውን ድጋፍ ገልጸዋል። “ጉዳዩ የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ብቻ ሳይሆን፣ የሰብዓዊነና የሰብዓዊ እሴቶች ጉዳይ ነው” ብለዋል ሞዲ።

ዜለንስኪ በመቀጠል ከአሜሪካው ፕሬዝደንት ጆ ባይደን እና ከአስተናጋጇ አገር ጠቅላይ ሚኒስትር ፉሚዮ ኪሺዳ ጋር እነደሚነጋገሩ ይጠበቃል።

XS
SM
MD
LG