በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አል ቡርሃን ዳጋሎን ከሥልጣን አነሱ


ጀኔራል አል ቡርሃን (በስተግራ) እና ጀኔራል ዳጋሎ (በስተቀኝ) (ፎቶ ፋይል ኤኤፍ ፒ)
ጀኔራል አል ቡርሃን (በስተግራ) እና ጀኔራል ዳጋሎ (በስተቀኝ) (ፎቶ ፋይል ኤኤፍ ፒ)

የሱዳኑ መሪ ጀኔራል አብደል ፋታህ አል ቡርሃን፣ ምክትላቸው የሆኑትን እና በአሁን ወቅት ግጭት ላይ ያሉትን የፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ መሪ ጀኔራል ሞሃመድ ሃምዳን ዳጋሎን ከስልጣን አንስተዋል።

በሌላ በኩል ደቡብ ሱዳን የዳጋሎን ወኪል ተቀብላ በማስተናገዷ ሱዳን ቁጣዋን ገልጻለች፡፡

የዳጋሎ ወኪል የሆኑት ዩሲፍ ኢሻ ከደቡብ ሱዳኑ ፕሬዝደንት ስልቫ ኪር እና ከኢጋድ ባለሥልጣናት ጋር መነጋገራቸውን የኤኤፍፒ ዘገባ አመልክቷል።

የሱዳን የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ ደቡብ ሱዳን የዳጋሎን ወኪል ተቀብላ ማነጋገሯን በጽኑ አውግዞ፣ የተቃውሞ ደብዳቤ መላኩን አስታውቋል።

ደቡብ ሱዳን በበኩሏ ለማንም ሳትወግን በኢጋድ ውስጥ ያላትን ሃላፊነት እየተወጣች መሆኑን የአገሪቱ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል። “ለማስታረቅ በሚደረግ ጥረት ውስጥ ሁሉንም ወገኖች በእኩል ማናገር አስፈላጊ ነው” ብሏል የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር መ/ቤቱ ባወጣው መግለጫ።

የሁለቱ ወገን ሠራዊቶች በካርቱም እና በዳርፉር ውጊያቸውን አሁንም እንደቀጠሉ ተዘግቧል። ግጭቱ ወደ ዳርፉር ተዛምቶ የታጠቁ ሲቪሎች ተሳትፈውበታል ተብሏል። ይህም ውጊያው የጎሳ መልክ እንዲይዝ ያደርጋል የሚል ስጋትን አስክከትሏል።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በግጭቱ ምክንያት ከሱዳን እየሸሹ ላሉ ዜጎች 22 ሚሊዮን ዶላር መመደቡን አስታውቋል። 1 ሚሊዮን የሚሆኑ ሰዎች እንደተፈናቀሉ ይገመታል።

XS
SM
MD
LG