በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የተመድ የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽነር ለሱዳን ስደተኞች የድጋፍ ጥሪ አቀረበ


የተመድ የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽነር ለሱዳን ስደተኞች የድጋፍ ጥሪ አቀረበ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:30 0:00

የተመድ የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽነር ለሱዳን ስደተኞች የድጋፍ ጥሪ አቀረበ

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እና አጋሮቹ፣ ለሱዳን ስደተኞች መርጃ የሚውል፣ የሦስት ቢሊዮን ዶላር ድጋፍ እንዲደረግ ዐዲስ ጥሪ አቀረቡ።

የተመድ የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽነር፣ ዐዲሱን ዓለም አቀፍ የድጋፍ ጥሪ፣ ከትላንት በስቲያ ረቡዕ፣ ግንቦት 9 ቀን 2015 ዓ.ም. ያቀረበው፣ በሱዳን ያለው ግጭት ሁለተኛ ወሩን በያዘበት ወቅት ነው፡፡

ዓለም አቀፍ ድጋፉ፣ በሱዳኑ ጦርነት ለተከበቡ ሚሊዮኖች እና ግጭቱን እየሸሹ ወደ አጎራባች ሀገራት በመሰደድ ላይ ለሚገኙ በመቶ ሺሕ ለሚቆጠሩ ፍልሰተኞች እንዲደርስ የታቀደ መኾኑ ተመልክቷል፡፡

በጦርነቱ ሳቢያ ካሉባቸው አካባቢዎች ዳግም የመፈናቀል ዕጣ የገጠማቸውና በድንበር ወደ ኢትዮጵያ በመግባት ላይ የሚገኙ የልዩ ልዩ ሀገራት ዜጎች፣ ከተጨናነቁት ጊዜያዊ መጠለያዎች ውስጥ የሚገኙበትን ኹኔታም ያስረዳሉ። ዘገባው የአሶሽየትድ ፕሬስ ነው አሉላ ከበደ ወደ ዐማርኛ መልሶታል።

XS
SM
MD
LG