በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በአረብ ሊግ ጉባኤ ላይ ሶሪያ ከ 12 ዓመታት በኋላ ተሳተፈች 


የሶሪያው ፕሬዘዳንት በሽር አል አሳድ እና የሳዑዲ አረቢያው ልዑል ባድር ቢን ሱልጣን
የሶሪያው ፕሬዘዳንት በሽር አል አሳድ እና የሳዑዲ አረቢያው ልዑል ባድር ቢን ሱልጣን

የሳዑዲው አልጋ ወራሽ ሞሃመድ ቢን ሳልማን፣ በጀዳ በመካሄድ ላይ ባለው የአረብ ሊግ ጉባኤ መክፈቻ ሥነ-ስርዓት ላይ ሶሪያንና ዩክሬንን እንኳን ደህና መጣችሁ ብለዋል።

የሶሪያው ፕሬዝደንት ባሻር አል አሳድ ከ 12 ዓመታት መታገድ በኋላ በጉባኤው ሲታደሙ፣ የዩክሬኑ ፕሬዝደንት ቮሎዲሚር ዜሌንስኪ ደግሞ ከሩሲያ ጋር ላለባቸው ጦርነት ድጋፍ ለማሰባሰብ በጉባኤው ላይ ድንገት ተገኝተዋል።

በሁለቱም አገሮች ላይ በሩሲያ የተፈጸመው የአየር ድብደባ ከፍተኛ ውድመት አስከትሏል። በሶሪያ ግን የሩሲያ ድብደባ የሚፈጸመው በአል አሳድ ጥያቄ ነው። በሥልጣን ላይ ለመቆየት እንደረዳቸው ይነገራል።

በርካታ የአረብ አገራት ከሩሲያ ጋር ያላቸውን ግኑኝነት አሁንም እንደጠበቁ ሲሆን፣ በዩክሬን ላይ በሚደረገው ጦርነትም ገለልተኛ አቋማቸውን እንዳሳዩ ነው።

የአረብ ሊግ ጉባኤው በሱዳን እና በሌሎችም አካባቢዎች በሚካሀዱት ግጭቶች ላይ ያተኩራል ተብሏል።

XS
SM
MD
LG