በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዜሌንስኪ በቡድን 7 ጉባኤ ላይ ለመገኘት ወደ ጃፓን ያቀናሉ 


ፎቶ ሮይተርስ (ሚያዚያ 18. 2023)
ፎቶ ሮይተርስ (ሚያዚያ 18. 2023)

የዩክሬኑ ፕሬዝደንት ቮሎዲሚር ዜሌኒስኪ በጃፓን በሚካሄደው የቡድን 7 አገራት ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ወደዚያው እንደሚያቀኑ የዩክሬን የጸጥታ ባለሥልጣናት አስታውቀዋል።

ዜሌንስኪ ወደ ጃፓን በሚያቀኑበት በዚህ ወቅት፣ ሩሲያ የዩክሬንን ከተሞች በአየር እና በሚስዬል መደብደቧን ቀጥላለች፡፡ የባክሙትን ከተማ ለመቆጣጠር የሚደረገው ከፍተኛ ፍልሚያም ቀጥሏል።

ዋና ከተማዋ ኪቭ ትናንት ማምሻውንም ኢራን ሰራሽ በሆኑ ድሮኖች ኢላማ ስትሆን አምሽታለች ተብሏል። በየዝነው የፈረንጆች ወር ለአስረኛ ግዜ መሆኑ ነው። ድሮኖቹ በሙሉ በአየር ላይ እንዳሉ መደምሰሳቸውን የዩክሬን ሠራዊት አስታውቋል።

የዩክሬን መከላከያ ሠራዊት በበኩሉ፣ ዛሬ ማምሻውን 16 የሚሆኑ ድሮኖችን እና አንድ ክሩዝ ሚሳኤልን መተው መጣላቸውን አስታውቋል። ቦታው የት እንደሆነ ከመግለጽ ግን ተቆጥቧል።

በሂሮሺማ ጃፓን የሚካሄደው የቡድን 7 አገራት ጉባኤ፣ በሩሲያ ላይ ጠንከር ያለ ቅጣት ለመጣል እንደሚመክር ይጠበቃል ተብሏል።

XS
SM
MD
LG