በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በብዙኃን መገናኛ የሴት ተንታኞች ተሳትፎ ዝቅተኛ መኾኑ ተገለጸ


በብዙኃን መገናኛ የሴት ተንታኞች ተሳትፎ ዝቅተኛ መኾኑ ተገለጸ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:07 0:00

በብዙኃን መገናኛ የሴት ተንታኞች ተሳትፎ ዝቅተኛ መኾኑ ተገለጸ። የ

  • የሴት ብዙኃን መገናኛ ባለሞያዎች መዘርዝር በሞያ ማኅበሩ ተዘጋጅቷል

የኢትዮጵያ የብዙኃን መገናኛ ባለሞያ ሴቶች ማኅበር፣ ሴቶች በዜና እና በመረጃ ምንጭነት ያላቸው ተሳትፎ፣ ከ12 በመቶ እንደማይበልጥ በጥናት መረጋገጡን አስታወቀ፡፡

የማኅበሩ የቦርድ ሊቀ መንበር ርብቃ ታደሰ፣ ለአሜሪካ ድምፅ ሲናገሩ፥ በብዙኃን መገናኛው ላይ ለሚታየው ዝቅተኛ የሴቶች ተሳትፎ፣ የተለያዩ ምክንያቶች እንደሚቀርቡ ገልጸዋል፡፡

በዚኹ ጉዳይ፣ ለአሜሪካ ድምፅ አስተያየት የሰጡ ጋዜጠኞችም፣ በልዩ ልዩ ርእሶች ዙሪያ መረጃ የሚሰጡ ሴት ባለሞያዎችን ማግኘት ከባድ እንደኾነ ተናግረዋል፡፡

የኢትዮጵያ የብዙኃን መገናኛ ባለሞያ ሴቶች ማኅበር፣ ይህን ችግር ለመቅረፍ ያግዛል ያለውን የሴት ባለሞያዎች መዘርዝር(የመረጃ ቋት) አዘጋጅቷል፡፡ ዘገባውን ሙሉ ዝርዝር ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

XS
SM
MD
LG