በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ባይደን በቡድን-7 ጉባኤ ላይ ለመገኘት ጃፓን ገብተዋል


በግራ በኩል የሚታዩት የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን፣ ከጃፓኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ፉሚዮ ኪሺዳ ጋራ ዛሬ ግንቦት 10 ቀን 2015 ዓ.ም እጅ ለእጅ ተጨባብጠው።
በግራ በኩል የሚታዩት የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን፣ ከጃፓኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ፉሚዮ ኪሺዳ ጋራ ዛሬ ግንቦት 10 ቀን 2015 ዓ.ም እጅ ለእጅ ተጨባብጠው።

በቡድን-7 ስብሰባ ላይ ለመካፈል ጃፓን የገቡት የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን፣ ከጃፓኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ፉሚዮ ኪሺዳ ተገናኝተው ተነጋግረዋል።

የዓለም መሪዎች፣ በዓለም የመጀመሪያው አቶሚክ ቦምብ በተጣለባት ሂሮሺማ በመሰባሰብ ላይ ሲኾኑ፣ ሩሲያ በዩክሬን ላይ የከፈተችው ጦርነት፣ የጉባኤው ዋና አጀንዳ ይኾናል፤ ተብሏል።

የቡድን-7 ጉባኤ ተሳታፊዎች፣ ወደ ሂሮሺማ በሚያቀኑበት ወቅት፣ ሩሲያ በዩክሬን መዲና ኪቭ ላይ የአየር ድብደባዋን አጧጡፋለች፡፡

የቡድን-7 ሀገራት መሪዎቹ፣ ከዩክሬኑ ፕሬዚዳንት ቮሎዲሚር ዜሌንስኪ ጋራ እንደሚመክሩ ዋይት ሐውስ አስታውቋል።የጃፓኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ፉሚዮ ኪሺዳ፣ ከፕሬዚዳንት ባይደን በተጨማሪ፣ ከእንግሊዙ ጠቅላይ ሚኒስትር ሪሺ ሱናክ ጋራ፣ ጉባኤው ነገ ከመጀመሩ በፊት ይገናኛሉ፤ ተብሏል።

የቡድን-7 አገራቱ፣ ከቻይና እየመጣ ያለውን የንግድ እና የመዋዕለ ነዋይ እገዳ እና ማዕቀብ አስመልክቶ እንደሚወያዩ ተጠቁሟል። አገራቱ ወደ ቻይና የሚልኩትን ሸቀጥ፣ እንዲሁም ቻይና ውስጥ የሚያፈሱትን መዋዕለ ነዋይ በመቆጣጠር እና በማገድ፣ የቻይናን የቴክኖሎጂ ፍጥነት እንዲያዘግም ለማድረግ እና በዓለም ያላትን የአቅርቦት የበላይነት ለመቀነስ የሚጥሩበትን መላ ይዘይዳሉ፤ ተብሏል።

XS
SM
MD
LG