በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በዓለም ለሞት ቅጣት አኀዝ ማሻቀብ ኢራንና ሳዑዲ አረቢያ ተወቀሱ


በዓለም ለሞት ቅጣት አኀዝ ማሻቀብ ኢራንና ሳዑዲ አረቢያ ተወቀሱ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:00 0:00

በዓለም ለሞት ቅጣት አኀዝ ማሻቀብ ኢራንና ሳዑዲ አረቢያ ተወቀሱ

በዓለም ላይ በሞት ፍርድ የሚቀጡ ሰዎች በከፍተኛ አኀዝ እያሻቀበ የሚታየው፣ በቀንደኞቹ የሕጉ አስፈጻሚዎች ኢራንና ሳዑዲ አረቢያ ምክንያት እንደኾነ፣ አምነስቲ ኢንተርናሽናል ገለጸ፡፡

እ.አ.አ. በ2022 የተመዘገበው የሞት ቅጣት አኀዝ፣ ከዚያ በፊት በነበሩት አምስት ዓመታት ውስጥ ከታየው ትልቁ መኾኑን፣ አምነስቲ ኢንተርናሽናል አስታውቋል።

ባለፈው ዓመት፣ በ20 አገሮች ውስጥ፣ 883 የሞት ቅጣቶች መመዘገባቸውን የጠቆመው የአምነስቲ ሪፖርት፣ ይህም ከቀደመው 2022፣ የ53 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱን አመልክቷል፡፡

ይኸው ሪፖርቱ፣ የሞት ቅጣት አኀዞች በምስጢር የሚያዙባትን ቻይናን እንደማያካትት፣ አምነስቲ ኢንተርናሽናል አክሎ አመልክቷል። ሄንሪ ሪጅዌል ከለንደን ያጠናቀረውን የዚኽን ዘገባ ዝርዝር ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

XS
SM
MD
LG