ተስፋ ማርያም ዳርጌ፣ ኮምቦልቻ ተወልዶ፣ መቐለ ያደገ ወጣት ነው፡፡ ከዩኒቨርሲቲ በኢኮኖሚክስ ከተመረቀ በኋላ፣ ቪድዮግራፊ እና የፊልም ሥራ ጥበብ በመማር፣ ላለፉት አምስት ዓመታት በሞያው ተሠማርቶ፣ ልዩ ልዩ ፊልሞችን በመሥራት ላይ ይገኛል፡፡
እስከ አሁን ድረስ የሠራቸው ከ10 በላይ አጫጭር ፊልሞች፣ በልዩ ልዩ መድረኮች ለእይታ በቅተውለታል፡፡ ተስፋ ማርያም፣ በዓለም የፊልም ዐውደ ትርኢቶች(ፌስቲቫሎች) በመወዳደርም፣ የተለያዩ ሽልማቶችን አሸንፏል፡፡
በቅርቡ “መዳረሻዬ የት ነው?” በሚል፣ በወጣቶች ስደት ላይ ትኩረት በአደረገ ፊልሙ፣ የአውሮፓ ኅብረት በአካሔደው ዓለም አቀፍ ውድድር አንደኛ በመውጣት አሸናፊ ኾኗል፡፡ ከዚያም ቀደም ሲል፣ በአውስትራሊያ በተደረገ የፊልም ዐውደ ትርኢት እንዲሁ፣ በአጭር ፊልም ውድድር አሸንፏል፡፡
/ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ያግኙ/