በ“ሰው ሠራሽ አስውሎት”(አርቲፊሺያል ኢንተሊጀንስ) በቀላሉ የሚፈበረኩ የሐሰት ፎቶዎች፣ ተንቀሳቃሽ ምስሎች እና ድምፆች፣ ድምፅ ሰጪዎችን በማሞኘት ውጤትን ሊያዛቡ ይችላሉ፤ ሲሉ የኮምፒዩተር መሐንዲሶች እና ወደ ቴክኖሎጂ - ጠቀስ - የፖለቲካ ጠበብት አስጠንቅቀዋል።
ያለብዙ ወጪ የሚፈበረኩት ሓሳዊ ምስሎች እና ድምፆች፣ ከሌሎች ሐሰተኛ መረጃዎች ጋራ በማኅበራዊ የትስስር መድረኮች በቀላሉ ስለሚሠራጩ፣ አደገኝነታቸው የከፋ እንደሚኾን ተመልክቷል።
“በሰው ሠራሽ አስውሎት”(አርቲፊሺያል ኢንተሊጀንስ)፣ የሰዎችን ድምፅ እና ምስል በቅጽበት እና በቀላል ወጪ አስመስሎ ሠርቶ፣ ከፍተኛ ተጽእኖ በሚፈጥረው የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴ በስፋት እና በፍጥነት ማሠራጨቱ፣ በምርጫ ዘመቻ ወቅት የሚታየውንና በመራጮች ግንዛቤ እና አቋም ላይ ቀላል የማይባል አሉታዊ ግፊት ያለውን የቅጥፈት ተረክ የከፋ ያደርገዋል፤ ተብሏል።
በአሜሪካ፣ በመጪው ዓመት ለሚካሔደው ምርጫ እና የምረጡኝ ዘመቻ ከፍተኛ ዕንቅፋት ይኾናል፤ የሚል ስጋት መፍጠሩን የአሶሺዬትድ ፕረስ ዘገባ አመልክቷል።