በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሱዳን በቤተ- ክርስቲያን ላይ በተፈጸመ ጥቃት አምስት ሰዎች ተጎዱ


STILL PHOTOGRAPHS OF PEOPLE WOUNDED IN CHURCH ATTACK
STILL PHOTOGRAPHS OF PEOPLE WOUNDED IN CHURCH ATTACK

በሱዳን ግጭቱ ቀጥሎ ባለበት ሁኔታ፣ በኦምዱርማን የሚገኝ ቤተ- ክርስቲያን ላይ ጥቃት ከተፈጸመ በኋላ አንድ ቄስን ጨምሮ 5 ሰዎች መጎዳታቸው ታውቋል፡፡ ተፋላሚ ወገኖቹ አንዱ ሌላውን ለጥቃቱ ተጠያቂ አድርገዋል፡፡

ሮይተርስ በላከው ምሥል ‘ማር ጊዮርጊስ’ በተባለ ቤተ ክርስቲያን ላይ በተፈጸመው ጥቃት የተጎዱ ሰዎች ታይተዋል፡፡

ጦር ሰራዊቱ ለጥቃቱ ፈጥኖ ደራሽ ኃይሉን ተጠያቂ ሲያደርግ፣ ፈጥኖ ደራሹ በበኩሉ ከጦር ኃይሉ ጋር ግኑኝነት አላቸው ያላቸውን አክራሪ ቡድኖችን ተጠያቂ አድርጓል፡፡

የጦር ኃይሉ ጠቅላይ አዛዥ አብደል ፋታህ አል ቡርሃን ባወጡት መግለጫ ፈጥኖ "ደራሽ ኃይሉ በቤተ-ክርስቲያኑ ምዕመናን ላይ ተኩስ ከፍቷል " ብለዋል።

በሱዳን ያለው ግጭት ለአምስተኛ ሳምንት ዛሬ ሰኞ እንደቀጠለ ሲታወቅ፣ እስከ አሁን 750 ሰዎች ሲሞቱ፣ በሺሕ የሚቆጠሩ ቆስለዋል፡፡ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ደግሞ ተፈናቅለዋል፡፡

XS
SM
MD
LG