No media source currently available
የሙዚቀኛ ዳዊት ፍሬው ኃይሉ ስርዓተ ቀብር ዛሬ ቤተሰቦቹ፣ ወዳጅ ዘመዶቹ፣ የሙያ አጋሮቹና አድናቂዎቹ በተገኙበት በመንበረ ፀባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተፈፅሟል፡፡ ዝነኛው የክላርኔት ሙዚቃ መሳሪያ ተጫዋች ዳዊት፣ በሙዚቃ መሳሪያ ብቻ የተቀነባበሩ አራት ኢንስትሩመንታል አልበሞችን በግሉ አሳትሟል፡፡ በተጨማሪም የዝነኛ አባቱን ፍሬው ኃይሉ ሙዚቃዎች በድምፁ በመጫወት የሚታወቅ ሲሆን በተለያዩ የውጭ ሀገራት በተዘጋጁ ኮንሰርቶች ሥራዎቹን አቅርቧል፡፡