በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሱዳን ተፋላሚዎች የሰብአዊ ረድኤት ተደራሽነት ስምምነት ተፈራረሙ


የሱዳን ተፋላሚዎች የሰብአዊ ረድኤት ተደራሽነት ስምምነት ተፈራረሙ
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:41 0:00

በሳዑዲ አረቢያ የወደብ ከተማ ጀዳ ላይ ለንግግር የተቀመጡት የሱዳን ተፋላሚ ኃይሎች ልዑካን፣ በሰብአዊ ረድኤት ተደራሽነት ላይ ያተኮረ ስምምነት ተፈራርመዋል።

የጦር ሠራዊቱ አዛዥ ጀነራል አብዱል ፋታሕ አል ቡርሃንና የፈጥኖ ደራሹ ኃይል አዛዥ ጀነራል መሐመድ ሃምዳን ዳጋሎ መልዕክተኞች የፈረሙት ስምምነት፣ የተኩስ አቁም ውል ባይኾንም፣ ወደ ትክክለኛ አቅጣጫ ሊያመራ የሚችል ርምጃ እንደኾነ፣ ባለሥልጣናት አመልክተዋል።

ስምምነቱ፣ ሁለቱ ተቀናቃኞች፣ ለሰላማዊው ሕዝብ የሰብአዊ ርዳታ አቅርቦት የሚተላለፍበት መንገድ እንዲመቻች ይጠይቃል፡፡ በግጭቱ ምክንያት የተቋረጡበት፥ የኤሌክትሪክ እና የውኃ መሠረታዊ አገልግሎቶች እንዲቀጠሉለትና ተፋላሚ ወገኖች በየሆስፒታሉ ያሉትን ታጣቂዎቻቸውን እንዲያስወጡ ያሳስባል። በውጊያው የተገደሉ ሰዎች ግብአተ መሬት በተገቢው ክብር እንዲከናወን የሚጠይቅ መኾኑ ተመልክቷል።

ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

XS
SM
MD
LG