በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ከሱዳን ወደ መተማ ለሚገቡ የሀገራት ዜጎች ዓለም አቀፍ የድጋፍ ጥሪ ቀረበ


ከሱዳን ወደ መተማ ለሚገቡ የሀገራት ዜጎች ዓለም አቀፍ የድጋፍ ጥሪ ቀረበ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:05 0:00

ከሱዳን ወደ መተማ ለሚገቡ የሀገራት ዜጎች ዓለም አቀፍ የድጋፍ ጥሪ ቀረበ

በኢትዮጵያ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ተወካይ እና የሰብአዊ ጉዳዮች አስተባባሪ ካትሪን ሱዚን ጨምሮ፣ የሌሎች የተባበሩት መንግሥታት ተቋማት ተወካዮችን ያካተተ ቡድን፤ በዐማራ ክልል የሱዳኑን ግጭት በመሸሽ ወደ መተማ እየገቡ ያሉ የልዩ ልዩ ሀገራት ሲቪሎችን በተመለከተ ውይይት አድርጓል።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብአዊ ርዳታ ማስተባበሪያ ቢሮ (OCHA) በአወጣው ሪፖርት፣ የዐማራ ክልል፣ በምዕራብ ጎንደር ዞን፥ በመተማ ከተማ የሚገኙ ሲቪሎችን ለመደገፍ፣ ወትሮውንም ውስን ከኾነው ግብአቱ ላይ በመቀነስ እየረዳ እንደሚገኝ አስታውቋል።

ይህም ኾኖ፣ መተማ እየገቡ ያሉ ዜጎችን ለመደገፍ የሚውል፣ 1ነጥብ3 ሚሊዮን ብር የሚያወጣ የሕክምና አቅርቦት፣ ለምዕራብ ጎንደር ዞን አስተዳደር መሰጠቱን ኦቻ ጠቁሟል።

በኢትዮጵያ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ተወካይ እና የሰብአዊ ጉዳዮች አስተባባሪ ካትሪን ሱዚ፣ ለመተማው ሰብአዊ እንቅሰቃሴ ቀጣይ ድጋፍ እንደሚደረግ ማረጋገጣቸውንም ሪፖርቱ ጠቅሷል።

በሌላ በኩል፣ በዐማራ ክልል የምዕራብ ጎንደር ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ቢክስ ወርቄ፣ የክልሉ መንግሥት፥ ከሱዳን ሸሽተው ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ የልዩ ልዩ ሀገራትን ዜጎች ተቀብሎ እያስተናገደ መኾኑን ገልጸው፣ ፍልሰተኞቹ፣ መተማ ላይ ለሚያደርጉት ቆይታ እና ሌሎች አስፈላጊ ድጋፎች፣ ወጪውን እየሸፈነ መሰንበቱን አስታውቀዋል፡፡

ዓለም አቀፉ የፍልሰት ድርጅት (IOM)፣ ፍልሰተኞችን ለማገዝ መጠለያዎችን እየገነባ ሲኾን፣ ዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ማኅበር ደግሞ ውኃ እያቀረበ መኾኑን፣ የምዕራብ ጎንደር ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ቢክስ ወርቄ ገልጸዋል። ሌሎች ዓለም አቀፍ ረጅ ድርጅቶችም፣ አስቸኳይ እና አስፈላጊ ቀሳቁሶችን እንዲያቀርቡ፣ ዋና አስተዳዳሪው ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ከሱዳን ሸሽተው በመተማ በኩል እየገቡ ያሉት የኢትዮጵያ፣ የኤርትራ እና የሱዳን ዜጎች ሲኾኑ፣ በቀን በአማካይ አንድ ሺሕ እንደሚደርሱ፣ አቶ ቢክስ አክለው ገልጸዋል፡፡

ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ያዳምጡ።

XS
SM
MD
LG