በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአረብ ሊግ ሶሪያን በአባልነት ዳግም ለመቀበል ወሰነ


የአረብ ሊግ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች እሁድ ዕለት ከአስር አመታት በኃላ ሶሪያን በአባልነት ለመቀበል የቀረበውን ውሳኔ ማፅደቃቸውን የሊጉ ቃል አቀባይ ገልጸዋል።
የአረብ ሊግ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች እሁድ ዕለት ከአስር አመታት በኃላ ሶሪያን በአባልነት ለመቀበል የቀረበውን ውሳኔ ማፅደቃቸውን የሊጉ ቃል አቀባይ ገልጸዋል።

የአረብ ሊግ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በዛሬው ዕለት ከአስር አመታት በኃላ ሶሪያን በአባልነት ለመቀበል የቀረበውን ውሳኔ ማፅደቃቸውን የሊጉ ቃል አቀባይ ገልጸዋል። ከፕሬዚዳንት ባሻር አል-አሳድ ጋር ያለውን ግንኙነት ወደ ወደነበረበት ለመመለስ የተጀመረውን ቀጠናዊ ግፊት ውሳኔው እንደሚያጠናክርም ተነግሯል ።

ውሳኔው የተላለፈው ካይሮ ውስጥ በሚገኘው የአረብ ሊግ ዋና መስሪያ ቤት በተደረገው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ዝግ ስብሰባ ላይ መሆኑን የዋና ጸሀፊው ቃል አቀባይ ጋማል ሮሺዲ አክለዋል ።

በ 2011 የአውሮፓዊያኑ ዘመን ሶሪያ የአረብ ሊግ አባልነት የተቋረጠው በአሳድ ላይ በተደረጉ የጎዳና ላይ ህዝባዊ ተቃውሞ እንስቃሴዎች ላይ ደም አፋሳሽ እርምጃ በመውሰዱ ብሎም ወደ አውዳሚ የርስ በርስ ጦርነት ማምራቱን ተከትሎ ነበር ። በወቅቱ በርካታ የአረብ ሀገራት ልዑካኖቻቸውን ከደማስቆ አስወጥተዋል።

በቅርቡ፣ ሳዑዲ አረቢያ እና ግብፅን ጨምሮ በርካታ የአረብ ሀገራት ከሶሪያ ጋር የላቀ ስፍራ ስፍራ ባላቸው ጉብኝቶች እና ስብሰባዎች አማካይነት ግኑኝነታቸውን ማደስ ጀምረዋል ። ሆኖም ኳታርን ጨምሮ አንዳንድ አባል ሀገራት ፣ ለሶሪያ ውስጥ ግጭት ፖለቲካዊ መፍትሄ ባልተሰጠበት ሁኔታ ግንኙነቶችን ወደ ነበሩበት ሁኔታ መመለስን ይቃወማሉ ።

ዘገባው የሮይተርስ ነው።

XS
SM
MD
LG