በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በቴክሳስ የገበያ ማዕከል በተፈጸመ የጅምላ ተኩስ ጥቃት  8 ሰዎች ተገደሉ


በቴክሳስ የገበያ ማዕከል በተፈጸመ የጅምላ ተኩስ ጥቃት 8 ሰዎች ተገደሉ፣ የጥቃት ፈጻሚው ህይወትም አልፏል ።
በቴክሳስ የገበያ ማዕከል በተፈጸመ የጅምላ ተኩስ ጥቃት 8 ሰዎች ተገደሉ፣ የጥቃት ፈጻሚው ህይወትም አልፏል ።

ቅዳሜ ዕለት አንድ ታጣቂ በዳላስ ቴክሳስ አቅራቢያ በሚገኝ የገበያ አዳራሽ ላይ ተኩስ ከፍቶ ስምንት ሰዎችን ሲገድል ሰባቱን ደግሞ ማቁሰሉን ባለስልጣናት ገለፁ። ባለሥልጣናቱ እንደተናገሩት ተኳሹ አሌን ፕሪሚየም አውትልስ በተሰኘው የገበያ አዳራሽ ውስጥ በነበረ የፖሊስ መኮንን በጥይት ተመትቶ ተገድሏል።


ፖሊስ ስለ ተጎጂዎቹ እና ስለ ተኳሹ ማንነት እስካሁን ምንም መረጃ አልሰጠም። ነገር ግን ከገበያ ማዕከሉ የወጡ ሰዎች እንደተናገሩት ከተጎጂዎቹ መካከል ህጻናት እንደሚገኙበት ይታመናል።

የቅዳሜው ክስተት በዚህ ዓመት ከተመዘገቡት የጅምላ ተኩስ ጥቃቶች የቅርብ ጊዜው ነው ። አሶሼትድ ፕሬስ ፣ዩኤስኤ ቱዴይ እና ኖርዝኢስት ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ባሰናዱት የመረጃ ቋት መሰረት በሳምንት አንድ ጊዜ የጅምላ ተኩስ ጥቃት እየደረሰ ይገኛል ።

XS
SM
MD
LG