በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዩክሬንን ሚሳዬል ክሪሚያ ውስጥ መታ መጣሏን ሩሲያ አስታወቀች


ፎቶ ኤፒ ሚያዚያ 6፣ 2023
ፎቶ ኤፒ ሚያዚያ 6፣ 2023

ዩክሬን ከፍተኛ የመልሶ ማጥቃት እርምጃ እንደምትወስድ በመነገር ላይ ባለበት በዚህ ወቅት፣ ሩሲያ ከዩክሬን የተተኮሰ ነው ያለችውን ባሊስቲክ ሚሳዬል ከክሪሚያ ሰማይ ላይ መትቼ ጥያለው ብላለች።

ሩሲያ ክሪሚያን ከ 9 ዓመታት በፊት ከዩሬን ቆርጣ ወደ ግዛቷ መጠቅለሏ ይታወሳል። በሚሳዬሉ የተጎዳ ሰውም ሆነ ንብረት የለም ሲሉ የክሪሚያ ገዢ ሆነው በሞስኮብ የተሾሙት ሰርጌይ አክስዮኖቭ ተናግረዋል።

በሌላ በኩል የሩሲያ ቅጥር ወታደራዊ ቡድን የሆነው ዋግነር አዛዥ ወታደሮቻቸው ተቆጣጥረው የሚገኙትን የባክሙት ከተማ ለቼቸኑ መሪ ራምዛን ካዲሮቭ ለማስረከብ ሞስኮብ ፍቃድ እንድትሰጣቸው ዛሬ ጠይቀዋል።

ወታደሮቻቸው ካለ በቂ መሣሪያ ስለሚዋጉ አላስፈላጊ ሕይወት እየከፈሉ በመሆናቸውና ከሩሲያ ወታደራዊ አዛዦች ትብብር ተነፍጎኛል በሚል ባክሙትን ከጥቂት ቀናት በኋላ ለቀው እንደሚወጡ የዋግነሩ መሪ የቭጌኒ ፕሪጎዚን ትናንት አስታውቀው ነብር።

በሌላ ዜና፣ ክሬምሊንን ይደግፋል የተባለና ዛካር ፕሪለፒን የተሰኘ ጸሃፊ በመኪና ላይ በደረሰ ፍንዳታ ጉዳት ከደረሰበት በኋላ ባለሥልጣናት የሽብር ምርመራ እንዲደረግ አዘዋል። በፍንዳታው የአንድ ሌላ ግለሠብ ሕይወት ማለፉም ታውቋል።

በፍንዳታው ሩሲያ ዩክሬንን ተጠያቂ አድርጋለች።

በርክሬምሊን ላይ ሊፈጸም የነበረ የድሮን ጥቃት አክሽፊያለሁ ስትል ሩሲያ በሣምንቱ መጀመሪያ ላይ አስታውቃ ነበር። የድሮን ጥቃት ሞከራው የመጣው ከዩክሬን ነው ስትል ሩሲያ አስታውቃ ነበር።

XS
SM
MD
LG