በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የእንግሊዙ ንጉስ ቻርለስ በዓለ-ሲመት ዛሬ  በደማቅ ሥነ-ስርዓት ተከናውኗል


ፎቶ ሮይተርስ
ፎቶ ሮይተርስ

የእንግሊዙ ንጉስ ቻርለስ ዛሬ ዘውዳቸውን ጭነዋል። በእንግሊዝ በዓለ-ሲመት ሲከናውን ከ 70 አመታት በላይ መሆኑ ነው። የንጉስ ቻርለስ እናት የሆኑት ንግስት ኤልሳቤጥ ለ70 ዓመታት ዙፋኑ ላይ ከቆዩ በኋላ ባለፈው ጳጉሜ ህይወታቸው ሲያልፍ ልጃቸው ቻርለስ ወዲያውኑ ዙፋኑን ወርሷል።

ንጉስ ቻርለስ 2.2 ኪሎ ግራም የሚመዝነውንና ከ እ.አ.አ 1661 ጀምሮ ጥቅም ላይ ውል የቆየው ዘውድ ተጭኖላቸዋል። በተለያዩ ወድ ጌጦች የተዋበ ነበር። ከኦፊሴላዊ ሥነ-ሥራዓቱ በኋላ የተለመደውና ከእርሳቸው በፊት የነበሩ ነገስታት የሚጭኑትን የዘወትር ዘውድ ጭነዋል።

ባለቤታቸው ካሚላም ዘውድ ጭነው፣ ለንጉሱ ጉንበስ በማለት አክብሮት አሳይተዋል።

የብዙዎች ጥያቄ የነበረው፣ በብዙ ጉዳዮች ከቤተሰቡ ጋር ተቃቅሮ በአሜሪካ ካሊፎርኒያ ከቤተሰቡ ጋር የሚኖረው የንጉሱ ሌላው ልጅ፣ የቀድሞው ልዑል ሃሪ በበዓለ-ሲመቱ ላይ ይገኝ ይሆን የሚለው የነበረ ቢሆንም፣ ሃሪ በበዓሉ ላይ ተገኝቷል። ታላቅ ወንድሙ ዊሊያም በጉልበቱ በመንበርከክ ለንጉስ አባቱ ታማኝነቱን አሳይቷል።

የበዓለ-ሲመቱ ሌሎች ክንዋኔዎች ነገም እንደሚቀጥሉ ታውቋል።

XS
SM
MD
LG