የወላይታ ዞን ሕዝበ ውሳኔ ሰኔ 12 ቀን 2015 ዓ.ም እንደሚካሄድ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ። የመራጮች ምዝገባ እና ድምፅ የመስጠቱ ሂደትም በአንደ ቀን እንደሚከናወን ቦርዱ ይፋ አድርጓል፡፡ በወላይታ ዞን የሚንቀሳቀሱ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ውሳኔ ሕዝቡ መካሔዱን ተቃውመዋል፡፡
ምርጫ ቦርድ ባለፈው ጥር ወር ተካሂዶ በነበረው ውሳኔ ሕዝብ፣ በወላይታ ዞን የተከናወነው የተጭበረበረ መኾኑን ይፋ አድርጎ ውሳኔ ሕዝቡ በድጋሚ እንደሚካሔድ መግለፁ ይታወሳል፡፡
ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ፡፡