በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሐሰተኛ መረጃ ሰብአዊ መብቶችንና ዴሞክራሲን አደጋ ላይ ጥሏል


ሐሰተኛ መረጃ ሰብአዊ መብቶችንና ዴሞክራሲን አደጋ ላይ ጥሏል
please wait

No media source currently available

0:00 0:11:40 0:00

በኢትዮጵያ በከፍተኛ ኹኔታ እየተሠራጩ ያሉ ሐሰተኛ መረጃዎች እና የጥላቻ ንግግሮች፣ ባለፉት ጥቂት ዓመታት ለተቀሰቀሱ የብሔር እና የሃይማኖት ግጭቶች፣ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ከማድረጋቸው በተጨማሪ፣ ሰብአዊ መብቶችን በማፈን ለዴሞክራሲ ትልቅ ጠንቅ እየኾኑ መምጣታቸውን፣ የብዙኃን መገናኛ ባለሞያዎች እና አጥኚዎች አስታወቁ።

በተለይ በማኅበራዊ መገናኛ ዘዴ የሚሠራጩ ሐሰተኛ መረጃዎች፥ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ማኅበራዊ ተሳትፎዎችን እየገደቡ መኾኑን ያሠመሩበት ባለሞያዎቹ፣ ማኅበረሰቡ ትክክለኛ መረጃ የማግኘት መብቱን በማፈን፣ ሰብአዊ መብቶችንና ዴሞክራሲን ለአደጋ ዳርገዋል፤ ብለዋል።

“ሐሳብን በነፃነት የመግለጽ መብት፣ የሰብአዊ መብቶች ሁሉ አንቀሳቃሽ ነው፤” በሚል መሪ ቃል፣ ዛሬ በመላው ዓለም የሚከበረውን የፕሬስ ነፃነት ቀን አስመልክቶ፣ ባለሞያዎቹን ያነጋገረቻቸው ስመኝሽ የቆየ ተከታዩን ዘገባ አሰናድታለች።

XS
SM
MD
LG