በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሶማልያ ዜጎቿን ከሱዳን ማውጣት ጀምራለች


ሶማልያ ዜጎቿን ከሱዳን ማውጣት ጀምራለች
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:45 0:00

ሶማልያ፣ በትጥቃዊ ፍልሚያ ከምትናጠው ሱዳን፣ ዜጎቿን ማስወጣት ጀምራለች።

ከትላንት በስቲያ እሑድ ምሽት፣ ከአንድ መቶ የሚበልጡ ሶማልያውያን፣ ከካርቱም በአውሮፕላን ሲወጡ፣ በቀጣዮቹም ቀናትም፣ ተጨማሪ ሶማልያውያንን ይዘው የሚወጡ አውሮፕላኖች እንደሚላኩ የሶማሊያ መንግሥት አስታውቋል።

በተለይ የሀገራቸው ሥርዐተ መንግሥት እና የትምህርት ሥርዐቱ በተንኮታኮተባቸው ዓመታት፣ በሱዳን ትምህርታቸውን ያጠኑ ሶማልያውያን ስብስብ፣ ኹኔታውን በልዩ ትኩረት እየተከታተለው ነው።

ሱዳን ስለ ሰጠቻቸው የትምህርት ዕድል ያመሰግኑት ሶማልያውያኑ፣ የሁለቱ ኃይሎች ትጥቃዊ ፍልሚያ ፈጥኖ እንደሚያበቃ ተስፋቸውን ገልጸዋል።

መሐመድ ሼኽ ኑር ከሞቃዲሾ ያስተላለፈውን ዘገባ ቆንጅት ታየ ወደ ዐማርኛ መልሳዋለች።

XS
SM
MD
LG