በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዩናይትድ ስቴትስ ሞዛምቢክን በፀረ ሽብር እንቅስቃሴዋ ማገዟን ትቀጥላለች


ዩናይትድ ስቴትስ ሞዛምቢክን በፀረ ሽብር እንቅስቃሴዋ ማገዟን ትቀጥላለች
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:24 0:00

ካቦ ዴልጋዶ በተባለው በነዳጅ ሀብት የከበረ ክፍለ ግዛቷ ከሚንቀሳቀሱ እስላማዊ ታጣቂዎች ጋራ እየተዋጋች ለምትገኘው ሞዛምቢክ ድጋፍ መስጠቷን እንደምትቀጥል ዩናይትድ ስቴትስ አስታውቃለች፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የውጭ ርዳታ ክፍል ዳይሬክተር ዳፍና ራንድ፣ በሞዛምቢክ ያደረጉትን የሦስት ቀናት ጉብኝት ባለፈው ማክሰኞ ሲያጠናቅቁ፣ ለቪኦኤ በሰጡት ቃለ ምልልስ፣ አገራቸው ለሞዛምቢክ የጸጥታ ድጋፍ መስጠቷን እንደምትቀጥል አረጋግጠዋል፡፡

ባለሥልጣኗ አክለውም፣ ከዓለም ባንክ ጋራ በመኾን፣ በታወከው የካቦ ዴልጋዶ አካባቢ፣ ትምህርት ቤቶችንና ሆስፒታሎችን በመገንባት እንደምትረዳ አስታውቀዋል፡፡

ቻርልስ ማንግዊሮ ከሞዛምቢክ ዋና ከተማ ከማፑቶ ያጠናቀረው ዘገባ ዝርዝሩን ይዟል፡፡

XS
SM
MD
LG