በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኢትዮጵያ ወጣቶች ፌስቲቫል በአዲስ አበባ ተጀምሯል


በአዲስ አበባ እየተካሄደ ባለው የኢትዮ-ጃዝ ፌስቲቫል ላይ የኢትዮጵያ ባህላዊ ተወዛዋዦች ትዕይንታቸውን ሲያቀርቡ - ሚያዚያ 21፣ 2015 ዓ.ም
በአዲስ አበባ እየተካሄደ ባለው የኢትዮ-ጃዝ ፌስቲቫል ላይ የኢትዮጵያ ባህላዊ ተወዛዋዦች ትዕይንታቸውን ሲያቀርቡ - ሚያዚያ 21፣ 2015 ዓ.ም

በዩናይትድ ስቴትስ የገንዘብ ድጋፍ የተዘጋጀ እና "ተነሳሱ፣ የወደፊት ዕጣ ፈንታችሁን ተቆጣጠሩ" በሚል መሪ ቃል የተሰናዳ የወጣቶች ፌስቲቫል ቅዳሜ እለት በአዲስ አበባ ተጀምሯል።

ለሁለት ቀናት የሚቆየው ይህ ፌስቲቫል የተዘጋጀው ለሁለት አመታት በሰሜን ኢትዮጵያ የተካሄደው ደም አፋሳሽ ጦርነት ካበቃ ከወራት በኃላ እና የኢትዮጵያ መንግስት ከኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ጋር የሰላም ንግግር ማካሄድ በጀመረበት ወቅት ነው።

በዚህ ፌስቲቫል ላይ ወደ 20 ሺህ የሚጠጉ ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የተውጣጡ ወጣቶች የሚሳተፉ ሲሆን በዝግጅቱ መክፈቻ ላይ ንግግር ያደረጉት በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ትሬሲ አን ጃኮብሰን ይህ አይነቱ ዝግጅት "የስራ እድል ለመፍጠር፣ ብድር ማግኘት የሚቻልባቸውን እድሎች ለማመቻቸት እና በመላው ኢትዮጵያ ለሚገኙ ወጣቶች የአመራር እና የጤና አጠባበቅ እድሎችን ለመፍጠር ያስችላል" ብለዋል።


በዝግጅቱ ላይ ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ ሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ኢርጎጌ ተስፋዬ በበኩላቸው"መንግስታዊ እና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት፣ ሌሎች የማህበረሰቡ አካላት እንዲሁም ወጣቶች እራሳቸው ለተለያዩ ችግሮች ተጋላጭ መሆናቸውን መረዳት አለባቸው" ያሉ ሲሆን "ያልተነካ አቅም መኖሩን ማወቅ እና አስፈላጊውን መፍትሄ ማቅረብ ከሁላችንም ይጠበቃል" ብለዋል።


በአዲስ አበባ እየተካሄደ በሚገኘው በዚህ ፌስቲቫል ላይ በኢትዮጵያ ከሚገኙት 17 ከተሞች የተውጣጡ ስራ ፈጣሪዎች ስራዎቻቸውን እያቀረቡ ሲሆን ጦርነቱ ባደረሰው ከፍተኛ ተፅእኖ ምክንያት ከትግራይ ክልል የመጡ ተወካዮች አለመኖራቸው ተገልጿል።

ሆኖም ለሚቀጥሉት አምስት አመታት በዩናይትድ ስቴትስ ዓለም አቀፍ ልማት ኤጀንሲ /ዩኤስኤአይዲ/ ድጋፍ የሚደረግለት ይህ ፌቲቫል፣ ግጭቱ ያደረሰው ጉዳት ግምገማ እንደተጠናቀቀ የትግራይ ክልል ተሳታፊዎችንም እንደሚያካትት ተጠቁሟል።

XS
SM
MD
LG