በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሱዳን ጦርነት ምክንያት የኩላሊት ዕጥበት ህክምና መስተጓጎል ያስጨነቃቸው ህሙማን


ዶሃ ኢንተርናሽናል ሆስፒታል አቅራቢያ፣ ካርቱም፣ ሱዳን እአአ ሚያዚያ 21/2023
ዶሃ ኢንተርናሽናል ሆስፒታል አቅራቢያ፣ ካርቱም፣ ሱዳን እአአ ሚያዚያ 21/2023

ሱዳን ውስጥ እየተካሄደ ያለው ጦርነት የሀገሪቱን ሆስፒታሎች አገልግሎት አመሰቃቅሏል።

በከባድ መሣሪያና በአየር ጥቃት ውጊያው ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ ነዋሪዎች ከቤታቸው ለመውጣት አልቻሉም። በድንገት በተቀሰቀሰው ውጊያ ምክንያት በየሆስፒታሉ የነበሩ ሐኪሞች እና አስታማሚዎች ለመውጣት ሌሎቹም ወደ ሥራቸው ሊገቡ አልቻሉም።

አሶሲየትድ ፕሬስ እንደዘገበው ጦርነቱ ከጀመረ ወዲህ የኩላሊት ዕጥበት ህክምና እየሰጠ ያለው አንድ 17 መሳሪያዎች ያሉት አህመድ ካሲም የተባለው ማዕከል ብቻ ነው።

በማዕከሉ የኩላሊት ዕጥበት ህክምና ላይ ከነበሩት ህሙማን መካከል አንዱ ባቱል ሻሪፍ" ማእከሉ ስለተዘጋ ለዘጠኝ ቀናት ህክምናውን ላገኝ አልቻልኩም። እዚህ ለመምጣት 90 ሚሊዮን የሱዳን ፓውንድ ማለት ወደ40 ዶላር መክፈል አለብኝ። ሰዉ ገንዘብ የለውም። እዚህ ይታከሙ የነበሩ ከወዲያኛው ቅዳሜ ወዲህ ያልመጡ አሉ። ደግሞም ከባድ በሽታ ነው። መንገዱን መክፈት አለባቸው" በማለት ተማጽነዋል።

ደከምን። ይቺን ሀገር እግዚአብሄር ይርዳት ይጠብቃት። እኛ በጣም ደክመናል።  ፖታሲየሙ ተጠራቅሞብናል። የኩላሊት ዕጥበት ያስፈልገናል። ባለስልጣናቱ የሆስፒታል ህክምና ለሚያስፈልጋቸው ህሙማን አንድ ነገር ያድርጉ"

"ደከምን። ይቺን ሀገር እግዚአብሄር ይርዳት ይጠብቃት። እኛ በጣም ደክመናል። ፖታሲየሙ ተጠራቅሞብናል። የኩላሊት ዕጥበት ያስፈልገናል። ባለስልጣናቱ የሆስፒታል ህክምና ለሚያስፈልጋቸው ህሙማን አንድ ነገር ያድርጉ" ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል።

የማዕከሉ የኩላሊት ህክምና ዳይሬክተር ታካሚዎቹ ወደማዕከሉ መጥተው ህክምናቸውን ለመቀጠል ባለመቻላቸው ህይወታቸው ለአደጋ ተጋልጧል ብለዋል።

"ህሙማኑ ሁለት ወይ ሶስት የኩላሊት ዕጥበት ከተቋረጠባቸው ሳምባቸው ውሃ ስለሚይዝ ሰማኒያ ከመቶ ህይወታቸው የማለፍ አደጋ ያጋጥማቸዋል" ሲሉ ዶክተር ታጅ ኤል ዲን ሥጋታቸውን ገልጸዋል።

XS
SM
MD
LG