በሱዳን የሚገኙ ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን ስደተኞች፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት፥ ከኻርቱም ለመውጣት እንዲያግዛቸው ተማፀኑ፡፡ በከተማዋ የሚሰማው የተኩስ ልውውጥ፣ ከትላንት ዛሬ ቀለል ቢልም፣ የጸጥታ ኹኔታው ግን፣ ለደኅንነት የሚያሰጋ መሆኑን ስደተኞቹ ገልጸዋል፡፡
የኢትዮጵያ መንግሥት፣ በሱዳን የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን ሁኔታ በመከታተል ላይ መኾኑን፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።
በሌላ በኩል፣ በኻርቱም የሚገኘው የመንግሥታቱ ድርጅት የስደተኞች ጉዳይ ኮሚሽንን ጨምሮ ልዩ ልዩ ዓለም አቀፍ ተቋሟት ቢሮዎች ዝግ ኾነዋል፡፡
ኤደን ገረመው፣ በአሁን ሰዓት፣ ከቤተሰቦቻቸው ጋራ በኻርቱም በመኖሪያ ቤት ውስጥ ተጠልለው ያሉ ስደተኞችን አነጋግራ ያሰናዳቸው ዘገባ ቀጥሎ ይቀርባል፡፡
ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።