በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ ለምዕራብ ኦሮሚያ ታጣቂዎች የሰላም ጥሪ አቀረቡ


ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ ለምዕራብ ኦሮሚያ ታጣቂዎች የሰላም ጥሪ አቀረቡ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:24 0:00

ዛሬ ወደ ነቀምቴ የተጓዙት፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፣ ከአራቱ የወለጋ ዞኖች ከተውጣጡ የማኅበረሰብ ክፍሎች ተወካዮች ጋራ ውይይት አድርገዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሕዝቡ፥ ሰላምን በማረጋገጥ ፊቱን ወደ ልማት እንዲያዞር ማስገንዘባቸው ተገልጿል። “ከኛ የተለየ ሃሳብ ያላቸው ሰዎች ከዛሬ ቀን ጀምሮ በሰላም መግባት ይችላሉ፤” ሲሉም ተደምጠዋል።

የኢትዮጵያ ፓርላማ “ሸኔ” በሚል በአሸባሪነት የፈረጀውና ራሱን የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት ብሎ የሚጠራው ቡድን በበኩሉ፣ ገለልተኛ የሆነ የሦስተኛ ቡድን አደራዳሪነትን ሲጠይቅ ቆይቷል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ግን፣ ከዚህ ጋራ በተያያዘ፣ በውይይቱ ላይ ያነሡት ነገር የለም።

ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

XS
SM
MD
LG