በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ጋና የኦክስፎርዱን የወባ መከላከያ ክትባት በመፍቀድ የመጀመሪያዪቱ አፍሪካዊት ሆነች


ጋና የኦክስፎርዱን የወባ መከላከያ ክትባት በመፍቀድ የመጀመሪያዪቱ አፍሪካዊት ሆነች
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:05 0:00

ጋና፣ የኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲ ሳይንቲስቶች፥ “ዓለምን የሚለውጥ” በሚል የሚያወድሱትን የወባ መከላከያ ክትባት ለመጠቀም በመፍቀድ የመጀመሪያዋ አፍሪካዊት አገር ሆናለች፡፡

ባላፈው ሳምንት፣ የኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲ በአወጣው መግለጫ፣ “R21” በሚል የጠራው ዐዲሱ የወባ መከላከያ ክትባት፣ በበሽታው ከፍተኛ የሞት አደጋ ለተጋረጠባቸው፣ ከአምስት እስከ 36 ወራት ዕድሜ ሕፃናት እና ጎልማሶች፣ ጥቅም ላይ እንዲውል፣ ከጋና ባለሥልጣናት ይሁንታ ማግኘቱን አስታውቋል፡፡

በትንኝ አስተላላፊነት የሚሠራጨው የወባ በሽታ፣ በየዓመቱ ከ600ሺሕ በላይ ሰዎችን እንደሚገድል ተነግሯል፡፡ ከዚህ ውስጥ አብዛኛዎቹ፣ ከሰሐራ በታች ባሉ የአፍሪካ አገሮች ውስጥ የሚገኙ ሕፃናት ናቸው፡፡

የጋና ብሔራዊ የወባ ቁጥጥር መርሐ ግብር ሓላፊ ዶ/ር ናና ያው ፔፕራ፣ “የኦክስፎርድ ክትባት በትክክለኛው ጊዜ ነው የመጣው፤” ሲሉ ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ፡፡

XS
SM
MD
LG