በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በትግራይ 2ነጥብ3 ሚሊዮን ሕፃናት ወደ ትምህርት ገበታ አልተመለሱም


በትግራይ 2ነጥብ3 ሚሊዮን ሕፃናት ወደ ትምህርት ገበታ አልተመለሱም
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:59 0:00

በሰሜን ኢትዮጵያ የተከሠተውን ግጭት ለማስቆም፣ በመንግሥት እና በህወሓት መካከል የሰላም ስምምነት ቢፈረምም፣ አኹንም፣ “ከ2ነጥብ3 ሚሊዮን በላይ ሕፃናት ወደ ትምህርት ገበታቸው አልተመለሱም፤” ሲል፣ የሕፃናት አድን ድርጅት /ሴቭ ዘ ችልድረን/ አስታወቀ፡፡

የድርጅቱ የኮሚዩኒኬሽን፣ የሚዲያ እና የአድቮኬሲ ሥራ ክፍል ሐላፊ ሕይወት እምሻው፣ ለአሜሪካ ድምፅ እንደተናገሩት፣ በአሁኑ ወቅት በመላው ኢትዮጵያ፣ ከ3ነጥብ5 ሚሊዮን በላይ ሕፃናት፣ ከትምህርት ገበታቸው ተፈናቀለው እንደሚገኙ ገልጸዋል፡፡

የትግራይ ትምህርት ቢሮ በበኩሉ፣ ከሚመለከታቸው አካላት ጋራ በመተባበር፣ በክልሉ፣ በቅርቡ ትምህርት ለማስጀመር ጥረት እየተደረገ ነው፤ ብሏል፡፡ የክልሉ ትምህርት ቢሮ ሓላፊ ዶ/ር ኪሮስ ጉዑሽ፣ ለአሜሪካ ድምፅ ሲናገሩ፣ በክልሉ፣ ወደ ትምህርት ቤት ለመግባት የሚጠባበቁ 2ነጥብ4 ሚሊዮን ተማሪዎች እንዳሉ ጠቅሰው፣ እነዚኽን ሕፃናት በልዩ ልዩ መንገዶች ትምህርት ለማስጀመር በመሥራት ላይ ናቸው፡፡

ለዚኽ ዕቅድ መሳካትም፣ የሚመለከታቸው አካላት ኹሉ፣ አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርጉ ሐላፊው ጥሪ አቅርበዋል፡፡

XS
SM
MD
LG