በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የጣራ ቆርቆሮ ሠርቀዋል በሚል የገንዘብ ሚኒስትሩ በቁጥጥር ሥር ዋሉ


ፎቶ ሮይተርስ (ሚያዚያ 10፣ 2023)
ፎቶ ሮይተርስ (ሚያዚያ 10፣ 2023)

ዝቅተኛ የኑሮ ደርጃ ላይ ለሚገኙ ሰዎች ቤት መሥሪያ የሚውል የጣራ ቆርቆሮ ሰርቀዋል በሚል የዩጋንዳው የገንዘብ ሚኒስትር አሞስ ሉጎሉቢ በቁጥጥር ሥር ውለዋል።

ካራሞጃ በተባለው አካባቢ ዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ ዜጎች ቤት መሥሪያ ሊውል የነበረውን ቆርቆር ስርቆት በተመለከተ 10 ሚኒስትሮች፣ 31 የምክር ቤት አባላትና ሌሎች 13 የመንግስት ባለሥልጣናትን እየመረመረ መሆኑን ፖሊስ አስታውቋል።

የዩጋንዳው ተቃዋሚ መሪ ባቢ ዋይን ፕሮጄውን በሚመሩት ሚኒስትሮች ላይ የተፈጸመው እሥር “መሸፋፈኛ” ነው በማለት፣ ለረጅም ግዜ አገሪቱን የመሩትን ዩዎሪ ሙሴቪኒንና መንግስታቸውን የከፋ ሙስና በመፈጸም ወንጅለዋል።

የሙዚቃ ሥራቸውን ወደጎን በመተው ፖለቲካ ውስጥ የገቡት ባቢ ዋይን ሙሴቪኒን ጨምሮ ጠቅላላ ካቢኔያቸው በስርቆት ወህኒ መረውድ ነበረባቸው ማለታቸውን ኤኤፍፒ ዘግቧል።

XS
SM
MD
LG