በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

“እየሱስን እንድታገኙ ተራቡ” ብሎ ህይወት እንዲጠፋ አድርጓል የተባለው በቁጥጥር ሥር ዋለ


ፎቶ ሮይተርስ (ሚያዚያ 15፣ 2023)
ፎቶ ሮይተርስ (ሚያዚያ 15፣ 2023)

“እየሱስን እንድታገኙ ተራቡ” በሚል አራት ሰዎችን እንዲሞቱ አድርጓል በሚል የተጠረጠረውን ግለሠብ በቁጥጥር ሥር ማድረጉን የኬንያ ፖሊስ አስታውቋል።

የ “መልካም ዜና ዓለም አቀፍ ቤ/ክርስቲያን” ተከታዮች የሆኑ 11 ሌሎች ሰዎች ወደ ሆስፒታል መወሰዳቸውን ፖሊስ ጨምሮ አስታውቋል። ሶስቱ ለህይወት አስጊ ሁኔታ ውስጥ መሆናቸው ታውቋል።

ሌሎች ተጎጂዎች ሊኖሩ እንደሚችሉ ፖሊስ ጨምሮ ገልጿል።

ማከንዚ ተንጊ የተባለው የቤተክርስቲያን መሪ በኬንያ ዳርቻ ባለ ጫካ “እየሱስን እንድታገኝ ተራቡ” ብሎ ተከታዮቹን መስሰብስቡን ጥቆማ የደርሰው ፖሊስ፣ አካባቢውን ሲያሥስ ተጎጂዎቹን ማግኘቱንና ግለሰቡንም በቁጥጥር ስር ማዋሉን የኤኤፍፒ ዘገባ አመልክቷል።

XS
SM
MD
LG