በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ፍንዳታና የአየር ድብደባ በካርቱም


 በካርቱም ሰማይ ላይ ዛሬ የተሰተዋለው ጭስ (ፎቶ ኤኤፍፒ ሚያዚያ 15፣ 2023)
በካርቱም ሰማይ ላይ ዛሬ የተሰተዋለው ጭስ (ፎቶ ኤኤፍፒ ሚያዚያ 15፣ 2023)

የሱዳን መዲና ካርቱም ዛሬ በአየር ድብደባ፣ በከባድ መሣሪያ ተኩስ እና በፍንዳታ ስትናጥ ውላለች።

በመደበኛ ሠራዊቱ እና አፋጣኝ የእገዛ ኃይል ወይም በምጻረ ቃሉ አር ኤስ ኤፍ በሚል በሚጠራው ኃይል መካከል የተኩስ ልውውጥ የተካሄደ ሲሆን እንዱ የሌላውን ወታደራዊ ሠፈር እንዳጠቃ የኤኤፍፒ ዘገባ አመልክቷል።

አር ኤስ ኤፍ የፕሬዝደንቱን ቤተ መንግስት እና የካርቱምን አየር ማረፊያ መቆጣጠራቸውን ቢገልጹም፣ ሠራዊቱ ሃሰት ነው ብሏል።

አገሪቱ ሙሉ ለሙሉ እንዳትፈርስ ለመከላከል ተኩስ በአስቸኳይ እንዲቆም የሲቪል መሪዎች ጥሪ አድርገዋል።

በካርቱም አየር ማረፊያ የተገደለውን ጨምሮ ሶስት ሲቪሎች መሞታቸውንና ዘጠኝ የሚሆኑ መቁሰላቸውን የሓኪሞች ኅብረት አስታውቋል።

ግጭቱ የመጣው በአገሪቱ ወታደራዊ መሪ አብደል ፈታህ አል ቡራንና ከእርሳቸው ቀጥሎ ባሉት ሞሃመድ ሃምዳን ዳግሎ መካከል አፋጣኝ የእገዛ ኃይል ወይም በምጻረ ቃሉ አር ኤስ ኤፍ የተሰኘው ወታደራዊ ቡድን ወደ መደበኛ ሠራዊት የሚቀላቀልበትን ሁኔታ በተመለከተ ለሣምንታት አለመግባባትና ውጥረት መከሰቱን ተከትሎ ነው። ሁለቱ መሪዎች ወደ ሲቪል መንግስት ሽግግር በሚደረግበት አካሄድ ላይም ስምምነት የላቸውም።

አር ኤስ ኤፍ በሞሃመድ ሃምዳን ዳግሎ የሚመራ ነው።

በካርቱም በሚገኘው የአር ኤስ ኤፍ ወታደራዊ ሠፈር ላይ የአየር ጥቃት ማካሄዱን ሠራዊቱ አስታውቋል።

በወታደራዊ መኪና የተጫኑ ታጣቂዎች ወደ ካርቱም አየር ማረፊያና ወደ ፕሬዝደንታዊው ቤተመንግስት እንዲሁም ሌሎች ቁልፍ ቦታዎች መግባታቸውን እማኞች መናገራቸውን ተከትሎ፣ አር ኤስ ኤፍ ቦታዎቹን እንደተቆጣጠረ አስታውቆ ነበር። ሠራዊቱ ይህን ውውድቅ በማድረግ ቦታዎቹ በሙሉ ቁጥጥር ሥር እንደሆኑ ይናገራል።

“ሁሉንም ወታደራዊ ቦታዎች እስከምንቆጣጠርና የሠራዊቱ አባላት እስከሚቀላቀሉን ድረስ ውጊያውን አናቆምም” ሲሉ የአር ኤስ ኤፍ አዛዥ የሆኑት ዳግሎ ለአል ጃዚራ መናገራቸውን ኤኤፍ ፒ በሪፖርቱ ጠቅሷል።

ጃንጃዊድ ሚሊሺያ ከተባከው ቡድን የወጣው አር ኤስ ኤፍ ከአሥር ዓመታት በፊት በወቁ የአገሪቱ መሪ በነበሩት ኦማር አልበሺር የተቋቋመና፣ በምዕራብ ዳርፉር ክልል ዓረብ ያልህኑ እዳጣን ማኅበረሰቦችን ለማጥቃት በመጠቀማቸው የጦር ወንጅል ፈጽመዋል የሚል ክስ ቀርቦባቸው ነበር።

XS
SM
MD
LG