በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የክልል ልዩ ኃይል አደረጃጀት እንደማይኖር ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ተናገሩ


የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ (ፎቶ ፋይል፡ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት)
የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ (ፎቶ ፋይል፡ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት)

የኢትዮጵያ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊል ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ከዛሬ ጀምሮ የክልል ልዩ ኃይል የሚባል አደረጃጀት እንደማይኖር ተናገሩ።

ኢታማዦር ሹሙ ከዛሬ ጀምሮ የክልል ልዩ ኃይል መዋቅር እንደማይኖር በብሔራዊ ቴሌዥቭዥን ጣቢያ ቀርበው በሰጡት ማብራሪያ፤ ከዚህ በኋላ በልዩ ኃይል ስም የሚንቀሳቀስና ግዳጅ የሚቀበል ኃይል እንደማይኖር ተናግረዋል።

ከዚህ በኋላ በኢትዮጵያ የሚኖረው ፤ መከላከያ ሠራዊት፣ ፌደራል ፖሊስ፣ የክልል መደበኛ ፖሊስ እና ሚሊሺያ ብዛ እንደሚኖር በማብራሪያቸው ገልፀዋል። ከዚህ ውጭ ያለው አደረጃጀት ከዚህ በኋላ ሕገ ወጥ ነው ብለዋል።

የሚመለከታቸው የሥራ ሓላፊዎች በተገኙበት፤ የክልል ልዩ ኃይሎችን በፌዴራል ኅይሎች ውስጥ መልሶ ማደራጀት በተመለከተ ግምገማ መካሄዱን ኢታማዦር ሹሙ ጨምረው ገልፀዋል።

አብዛኛው ሥራ መጠናቀቁን ገልፀው ከዚህ በኋላ የሚቀረው የልዩ ኃይል አባላቱን ወደየ ምድባቸው ማጓጓዝ እና ለገቡት ደግሞ ሥልጠና መስጠት መኾኑን ተናግረዋል።

“የክልል ልዩ ኃይሎች እንደገና በመደራጀታቸው ኅብረ ብሄራዊ ጠንካራ የጸጥታ ተቋም ይገነባል” ያሉት ኢታማዦር ብርሃኑ

"ኢትዮጵያ ከነበረችበት የጸጥታ ችግር በከፍተኛ ሁኔታ ተመንጭቃ እየወጣች ነው" ያሉት ብርሃኑ ጁላ የፀጥታው ኹኔታ እየተስተካከለ በመኾኑ ወደ ሚፈለገው ደረጃ እየተሄደ ነው ብለዋል።

የክልል ኃይሎችን አደረጃጀት ለመቀየር ካስገደዱት ጉዳዮች መካከል “የክልል ልዩ ኃይሎች አደረጃጀት ህጋዊ አለመሆን፣ በክልሎች መካከል እንደ ስጋት መተያየት እንዲሁም ችግሮችን በኃይል ለመፍታት የሚደረገው እንቅስቃሴ” መሆናቸውን ፊልድ ማርሻሉ ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ መንግሥትን፣ የክልሎች ልዩ ኃይሎች መዋቅራዊ ለውጥ ውሳኔ በመቃወም፣ በአማራ ክልል ባለፈው ሳምንት ተቃውሞ ተቀስቅሶ የሰዎች ሕይወት ተፍቷል።

የኢትዮጵያ መንግሥት፣ የክልሎች ልዩ ኃይሎችን መልሶ ለማደራጀት የጀመረው ፕሮግራም፣ ሰብአዊ መብቶችን አደጋ ላይ በማይጥል አሠራር እንዲተገበር የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን አሳስቦ ነበር።

XS
SM
MD
LG