ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ፣ በወረቀት ይወጡ ከነበሩና በኋላም በመካነ ድር ከቀጠሉት የኅትመት ውጤቶች መካከል፣ መሠረቱን በኒውዮርክ ያደረገው ታዲያስ መጽሔት፣ 20ኛው ዓመቱን በማክበር ላይ ይገኛል፡፡
እንዲህ እንደ ዛሬው፣ የማኅበራዊ ብዙኃን መገናኛ እና ዲጂታል ኅትመት አማራጮች፣ በዐይነትም በመጠንም ሳይበራከቱ እና ሳይስፋፉ በፊት፣ ቀድመው ወደ ገጸ ድር ከወጡት መካከል ታዲያስ አንዱ ነው፡፡
የመሥመር-ላይ-መጽሔቱ፣ ከኢትዮጵያ ውጭ የሚኖሩ፣ ዕውቅ እና ሞያተኛ ትውልደ ኢትዮጵውያንን ማስተዋወቅን ጨምሮ የማኅበረሰቡን ልዩ ልዩ ውሎዎችንና ዝግጅቶችን ሲዘግብ መቆየቱን፣ የታዲያስ መሥራች፣ ባለቤት እና ዋና አዘጋጅ አቶ ሊበን ኤቢሳ፣ ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል።
ለመኾኑ፣ የመጽሔት ዝግጅቱን ከወረቀት ወደ ዲጂታል ኅትመት ማሸጋገሩ ምን ይመስላል? ሚዲያው እና ቴክኖሎጂውስ የወደፊት ምሪቱ ወዴት ነው? በእነዚኽ ነጥቦች ላይ፣ ከአቶ ሊበን ጋራ ቆይታ አድርገናል፡፡
ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ይከታተሉ።