በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ተመድ ለሶማልያ ከፍተኛ ዓለም አቀፍ ርዳታ ጠየቀ


ፎቶ ፋይል፡ - ልጆቿን ይዛ የምትታየው ሃዲቅ አብዱል መሀመድ መጋቢት 15 ቀን 2015 ዓ.ም ከሶማሊያ ወጣ ብሎ በሚገኝ የተፈናቃዮች ካምፕ ውስጥ ከአሶሼትድ ፕሬስ ዘጋቢዎች ጋር ቃለ ምልልስ በምታደርግበት ወቅት።ባደረገው
ፎቶ ፋይል፡ - ልጆቿን ይዛ የምትታየው ሃዲቅ አብዱል መሀመድ መጋቢት 15 ቀን 2015 ዓ.ም ከሶማሊያ ወጣ ብሎ በሚገኝ የተፈናቃዮች ካምፕ ውስጥ ከአሶሼትድ ፕሬስ ዘጋቢዎች ጋር ቃለ ምልልስ በምታደርግበት ወቅት።ባደረገው

የተባበሩት መንሥግታት ዋና ጸሐፊ አንቶንዮ ጉተሬዥ፣ ለሶማልያ፥ “ከፍተኛ ዓለም አቀፍ ድጋፍ” እንዲደረግ ተማፀኑ፡፡ዋና ጸሐፊው ተማፅኗቸውን ያሰሙት፣ በዐሥርት ዓመታት ውስጥ ከፍተኛ ነው ለተባለው የድርቅ አደጋ የተጋለጠቸውን ምሥራቅ አፍሪካዊቱን አገር በጎበኙበት ወቅት ነው፡፡

ለከፍተኛ ሰብአዊ ችግር የተጋለጠችው ሶማልያ፣ በተመሳሳይ ወቅት አደገኛ የኾነውን የሽብር እንቅስቃሴ እየተዋጋች መኾኑን ዋና ጸሐፊው ተናግረዋል፡፡ጉተሬዥ፣ ከሶማልያው ፕሬዚዳንት ሐሰን ሼኽ መሐሙድ ጋራ በመኾን፣ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫቸው፣ “አገሪቱ በገጠሟት ሰብአዊ ችግሮች የተነሣ፣ ከፍተኛ የኾነ ዓለም አቀፍ ርዳታ እንደሚያስፈልግ የሚያሳስበውን የማስጠንቀቂያ ደወል ለማሰማት እዚኽ ተገኝቻለኹ፤” ብለዋል፡፡

የተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸሐፊ፣ በዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያው ሲደርሱ፣ በሶማልያ እና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ከፍተኛ ባለሥልጣናት ሞቅ ያለ አቀባበል ተደርጎላቸዋል፡፡ በጉብኝቱ ወቅት፣ በርካታ የሞቃዲሾ አካባቢዎች ተዘግተው እና የሕዝብ ትራንስፖርት እንቅስቃሴዎች ተገድበው መቆየታቸው ተነግሯል፡፡

የሶማልያ ፕሬዚዳንት መሐሙድ፥ በአገሪቱ፣ ከፍተኛ የሰብአዊ ቀውስ ፈተናዎች እና የፀረ ሽብር ጦርነት እየተባባሰ በሚገኝበት ወቅት፣ ታሪካዊ ነው ያሉትን ጉብኝት በማድረጋቸው ዋና ጸሐፊውን አመስግነዋል፡፡

ፕሬዚዳንት መሐሙድ አያይዘውም፣ “ይህ ጉብኝት፣ አገሪቱን ለመገንባት እና ለማረጋጋት በያዝነው ዕቅድ፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሙሉ ለሙሉ እንደሚደግፈን አረጋግጦልናል፡፡ አገሪቱን ነፃ የማውጣቱንና እርቅ የመፍጠሩን ሒደት የተሟላ ለማድረግ፣ የሶማልያ ዜጎች አሁን ድረስ የገጠሟቸውን ችግሮች እና ፈተናዎች እንዲሚወጡ እንተማመናለን፤” ብለዋል፡፡

የምግብ ዋስትና ጠበብቶች፣ በታሪክ አስከፊ የኾነው የሶማልያ ድርቅ፣ በአገሪቱ ውስጥ ለተራቡት ከስድስት ሚሊዮን በላይ ሰዎች ሕይወት፣ አሁንም “እጅግ አደገኛ” መኾኑን ይናገራሉ፡፡

ከምሥራቅ አፍሪካው አልቃዒዳ ጋራ ግንኙነት ያለውንና በሺሕዎች የሚቆጠሩ ተዋጊዎችን ካሳለፈው አልሻባብ ጋራ በመዋጋት ላይ የምትገኘው ሶማልያ፣ ለከፍተኛ የደኅንነት ችግር የተጋለጠች መኾኑም ተመልክቷል፡፡

XS
SM
MD
LG