በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአማራ ክልል ልዩ ኃይልን መልሶ የማደራጀት ውሳኔን የሚቃወሙ ሰልፎች ተካሔዱ


የአማራ ክልል ልዩ ኃይልን መልሶ የማደራጀት ውሳኔን የሚቃወሙ ሰልፎች ተካሔዱ
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:32 0:00

የአማራ ክልል ልዩ ኃይልን መልሶ የማደራጀት ውሳኔን የሚቃወሙ ሰልፎች ተካሔዱ

መንግሥት፣ የአማራ ክልል ልዩ ኃይል አባላትን በልዩ ልዩ የጸጥታ ተቋማት በማስገባት መልሶ ለማደራጀት የያዘውን ፕሮግራም የተቃወመ ሰልፍ ዛሬ በደሴ ከተማ ተካሄደ፡
የአማራ ክልል በየአቅጣጫው የጸጥታ ስጋት ተጋርጦበት ያሉት ሰልፈኞቹ ፣ የልዩ ኃይልን መዋቅር አፍርሶ የሠራዊቱን አባላት ወደ ልዩ ልዩ የጸጥታ ተቋማት በማስገባት ዳግም ለማደራጀት ያሳለፈው ውሳኔ፣ “ተገቢነት የለውም” ሲሉ፣ ዛሬ በአካሔዱት የተቃውሞ ሰልፍ አስታውቀዋል፡፡
በአብዛኛው የአማራ ክልል ዋና ዋና ከተሞች፣ ባንኮችን ጨምሮ የመንግሥት ሥራ እና የግል ንግድ እንቅስቃሴዎች ለተገልጋዮች ዝግ ኾነው ውለዋል፡፡ አስተያየታቸውን ለቪኦኤ የሰጡ የከተማዋ ነዋሪዎች፣ ሃይማኖታዊ እና ሕዝባዊ በዓላትን ተንተርሶ በተደጋጋሚ እየተቀሰቀሱ ያሉ አለመረጋጋቶች እንዳሳሰባቸው ገልጸዋል፡፡ ዛሬ በከተማው ሊካሄድ ቀጠሮ ተይዞለት የነበርው ሰልፍ ተሰርዟል።

XS
SM
MD
LG