በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ቱኒዚያ ውስጥ በመቶዎች የተቆጠሩ ተቃዋሚዎች ሰልፍ አካሄዱ


ፋይል - በቱኒዚያ የሚገኘው የመዳን ግንባር ተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች እና የፕሬዝዳንቱ ተቺዎች መታሰራቸውን ተከትሎ በመጋቢት ወር ተካሂዶ በነበረ የተቃውሞ ሰልፍ ላይ የፓርቲው ደጋፊዎች ባንዲራ ሲያውለበልቡ ይታያሉ።
ፋይል - በቱኒዚያ የሚገኘው የመዳን ግንባር ተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች እና የፕሬዝዳንቱ ተቺዎች መታሰራቸውን ተከትሎ በመጋቢት ወር ተካሂዶ በነበረ የተቃውሞ ሰልፍ ላይ የፓርቲው ደጋፊዎች ባንዲራ ሲያውለበልቡ ይታያሉ።

ቱኒዚያ ዋና ከተማ ቱኒዝ ውስጥ ትናንት ዕሁድ ብዙ መቶ ሰዎች የተቃውሞ ሰልፍ አካሂደዋል፡፡ ሰልፉን ያካሄዱት የፕሬዚደንት ካዪስ ሰኢድ መንግሥት ያሰራቸውን ወደሃያ የሚሆኑ ተቃዋሚዎች እንዲፈታ በመጠየቅ መሆኑ ተዘግቧል፡፡

የፈረንሳይ የዜና ወኪል እንደዘገበው ሦስት መቶ የሚሆኑት ሰልፈኞች የቱኒዝያን ባንዲራ እና የፕሬዚደንቱን ተቃዋሚዎች ፎቶዎች የያዙ ትላልቅ ሰሌዳዎችን አንግበው ወጥተዋል፡፡

ካነገቧቸው ምስሎች መካከል የፖለቲካ ሰዎች፣ የቀድሞ ሚኒስትሮች፣ ነጋዴዎች የሰራተኛ ማህበራት መሪዎች እና በቱኒዥያ እጅግ ተወዳጅ የሆነው ሞዛይክ ኤፍ ኤም ራዲዮ ጣቢያ ባለቤት ፎቶዎች ይገኙባቸዋል፡፡

እ.አ.አ በ2021 የመንግሥት ስልጣን ጠቅልለው የያዙት ፕሬዚደንት ካዪስ የመንግሥት ጸጥታ ለማወክ የሚያሴሩ ሽብርተኞች ብለዋቸዋል፡፡

አምነስቲ ኢንተርናሽናል እና የአገር ውስጥ የሰብዐዊ መብት ቡድኖች በበኩላቸው በመሰረተ ቢስ ክስ የተያዙት እስረኞች በአስቸኳይ መፈታት አለባቸው ሲሉ አሳስበዋል፡፡

XS
SM
MD
LG