በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

እራሱን አቃጥሎ የሞተ ያስመሰለው እስረኛ ካመለጠበት ተያዘ


ፎቶ ኤፒ (መጋቢት 29፣ 2023)
ፎቶ ኤፒ (መጋቢት 29፣ 2023)

በደቡብ አፍሪካ ባለፈው ዓመት ግንቦት ወር ላይ የሞተ አስመስሎ ከእስር ቤት ያመለጠው ፍርደኛ ትናንት ዓርብ ታንዛኒያ ውስጥ ተይዟል።

የግለሰቡ በቅጥፈት የሞተ መስሎ ከእስር ቤት ማምለጡ የአገሪቱን ባለሥልጣናት ያሳፈረ ጉዳይ ሆኖ ነበር።

ታቦ ቤስተር አስገድዶ በመድፈር ጥፋተኛ ተብሎ ከወረደበት በግል የሚተዳደር ወህኒ ቤት ባለፈው ዓመት የሞተ መስሎ ቢወጣም፣ የደቡብ አፍሪካ ፖሊስ ስለ ጉዳዩ ያወቀው ግን ባለፈው ወር ነበር።

የደቡብ አፍሪካው የፍትህ ሚኒስትር ሮናልድ ላሞላ ዛሬ እንዳስታወቁት፣ ቤስተር ትናንት ማምሻዉን ከፍቅረኛውና ከአንድ ሌላ ግለሰብ ጋር ሳለ በታንዛኒያ የጸጥታ ኃይሎች ተይዟል።

ቤስተር ባለፈው ዓመት እራሱን በእሳት አቃጥሎ የሞተ አስመስሎ ንበር ያመለጠው። ፖሊስ ባለፈው ወር ባደረገው የዘረመል ማጣራት በእሳት የተለበለበው ሌላ ግለሰብ መሆኑን ደርሶበታል። በእሳት ተቃጥሎ የሞተው ግለሰብ ማንነት እስከ አሁን አለመታወቁን ፖሊስ አስታውቋል።

“የፌስቡክ አስገድዶ ደፋሪው” በመባል የሚታወቀው ቤስተር፣ ግለሰቦችን በማህበራዊ ሚዲያ ካማለለ በኋላ፣ አስገደዶ መድፈሩና መዝረፉ ታውቋል። ቢያንስ የአንድ ግለሰብን ሕይወት እንዳጠፋም የኤኤፍ ፒ ዘገባ አመልክቷል።

XS
SM
MD
LG