በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አሜሪካ ለታይዋን ተጨማሪ ወታደራዊ መሣሪያ ልትልክ ነው


ማይክል ማኮል - በአሜሪካ ተወካዮች ም/ቤት የውጪ ጉዳይ ኮሚቴ ሰብሳቢ (ፎቶ ሮይተርስ ሚያዚያ 7፣ 2023)
ማይክል ማኮል - በአሜሪካ ተወካዮች ም/ቤት የውጪ ጉዳይ ኮሚቴ ሰብሳቢ (ፎቶ ሮይተርስ ሚያዚያ 7፣ 2023)

ቻይና በታይዋን ድንበር ዙሪያ የሶስት ቀናት ልምምድ በጀመረችበት በዛሬው ዕለት፣ በታይዋን የሚገኙ አንድ የአሜሪካ ም/ቤት አባል የቻይናን ጠብ አጫሪነት ለመግታት አሜሪካ በአስቸኳይ ተጨማሪ መሣሪያዎችን እንደምትልክ ዛሬ አስታውቀዋል።

በተወካዮች ም/ቤት የውጪ ጉዳይ ኮሚቴ ሰብሳቢ የሆኑት ማይክል ማኮል እንዳሉት አሜሪካ ለታይዋን ወታደራዊ ሥልጠና በመስጠት እንዲሁም የጦር መሣሪያ በማቅረብ ትተባበራለች።

ታይፔ በጒብኝት ላይ የሚገኙት ማኮል አሜሪካ ለታይዋን ድጋፍ እነድምታደርግና ድጋፉንም በአፋጣኝ እንድምትፈጽም አስታውቀዋል።

የቻይና ጦር በበኩሉ ዛሬ እንዳስታወቀው በታይዋን ዙሪያ የሚደረገው ልምምድ ለደሴቲት ነጻነት ለቆሙ ኃይሎች እንዲሁም የውጪ ተባባሪዎች ማስጠንቀቂያ ነው።

በዎል ስትሪት ጆርናል ባለፈው ሕዳር የወጣ ሪፖርት እንደጠቆመው አሜሪካ ለታይዋን 18.7 ቢሊዮን ዶላር የሚገመት መሣሪያ ሸጣለች።

XS
SM
MD
LG