በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በማሊ የጋዜጠኛው መሠወር


በማሊ የፕረስ ነጻነት ቀን ተሳታፊዎች (ፎቶ ፋይል - ቪኦኤ)
በማሊ የፕረስ ነጻነት ቀን ተሳታፊዎች (ፎቶ ፋይል - ቪኦኤ)

በሁንታ በምትመራው ማሊ አንድ ጋዜጠኛ በእስር ላይ የሚገኝን ሌላ የሙያ አጋሩን ከእስር እንዲለቀቅ የሚጠይቅ ጋዜጣዊ መግለጫ እንዲሰጥ ካደረገ በኋላ የገባበት አልታወቀም።

ከትናንት በስቲያ ሐሙስ ጋዜጣዊ መግለጫው ላይ ከተሳተፈ በኋላ ቤተሰቡም ሆነ የሚሰራበት ድርጅት ባልደረቦች ሊያገኙት እንዳልቻሉ “ስብስብ ለሪፐብሊኳ ልማት” የተሰኘው የአሊዩ ቱሬ ተቋም አስታውቋል። ለማግኘት ያደረጉት ሙከራም አለመሳካቱ ታውቋል።

ቱሬ ከእስር እንዲለቀቅ ጥሪ ሲያደርግለት የነበረው ባልደረባው ሞሃመድ ባቲሊ፣ በእስር ላይ ሳሉ ባለፈው ዓመት ሕይወታቸው ያለፈው የቀድሞ የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር “ግድያ ተፈጽሞባቸዋል” ብሎ ባለፈው ወር ሪፖርት ካደረገ በኋላ በእስር ላይ ይገኛል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ አምነስቲ ኢንተርናሽናል ቡርኪና ፋሶ በመገናኛ ብዙሃን ላይ የምታደርገውን ጥቃት እንድታቆም ጠይቋል።

ቡርኪና ፋሶ የሚገኙ የፈረንሳይ ጋዜጠኞች ባለፈው ሣምንት አገር ለቀው እንዲወጡ ተደርጓል። የራዲዮ ፍራንስ ኢንተርናሽናል እና የፍራንስ 24 ስርጭቶችም እንዲቋረጡ ተደርጓል።

XS
SM
MD
LG