በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በአፍሪካ የጂሃዲስቶችን እንቅስቃሴ ለመግታት አሜሪካ ድጋፍ ልታደርግ ነው


የቶጎ ወታደር በጥበቃ ላይ (ፎቶ ፋይል ኤኤፍፒ)
የቶጎ ወታደር በጥበቃ ላይ (ፎቶ ፋይል ኤኤፍፒ)

በአይቮሪኮስት፣ ቤኒን እና ቶጎ የሚታየው የጂሃዲስቶች ሁከት ወደ ምዕራብ አፍሪካ እንዳይዛመት አሜሪካ የረጅም ግዜ ድጋፍ ለማግኘት ዝግጅት ላይ መሆኗን አንድ ባለሥልጣን አስታውቁ።

ባለሥልጣኑ ለአሶስዬትድ ፕረስ እንደተናገሩት፣ የሩሲያ ቅጥር ወታደራዊ ቡድን የሆነው ዋግነርን እንቅስቃሴ ለመግታት የምዕራባውያን ድጋፍ አስፈላጊ ነው። በአሜሪካ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር የምዕራብ አፍሪካ ሃላፊ ማይክል ሂዝ እንዳሉት ስጋቱ እያደገ የመጣና አገራቱ ከዚህ በፊት ገጥሟቸው የማያውቅ ነው።

በቀጠናው ጉብኝት አድርገው በቅርቡ የተመለሱት ሃላፍው ጨምረው እንዳሉት አሜሪካ አገራቱ የሚያስፈልጋቸውን የድጋፍ ዓይነት በመለየት ላይ ነች።

ሩሲያ በፈረንሳይኛ ተናጋሪ አፍሪካ አገሮች በኩል የሚታየውንና ቅኝ ግዛት ያስከተለውን ቅሬታ በመጠቀም ሃስተኛ መረጃ በማሰራጨትና ዋግነር ቡድንን በመጠቀም አገራቱን እያወከች ነው ስትል አሜሪካ ትከሳለች።

XS
SM
MD
LG