በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአማራ ክልላዊ መንግሥት ለ“አገው ዴሞክራዊ ንቅናቄ” የሰላም ጥሪ አቀረበ


የአማራ ክልላዊ መንግሥት ለ“አገው ዴሞክራዊ ንቅናቄ” የሰላም ጥሪ አቀረበ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:56 0:00

· “ችግሩ የሚፈታው በድርድር እንጂ በሽምግልና አይደለም” - አዴን

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት፣ በዋግ ኽምራ ዞን ኹለት ወረዳዎች እየተንቀሳቀሰ ለሚገኘው “የአገው ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ”፣ የሰላም ጥሪ ማቅረቡን አስታወቀ፡፡

የክልሉ ሰላም እና ጸጥታ ቢሮ ሓላፊ አቶ ደሳለኝ ጣሰው እንደተናገሩት፣ በዋግ ኽምራ ዞን በአበርገሌ እና በፃግብጂ አካባቢ እንደሚንቀሳቀስ ለጠቀሱትና “አገው ሸንጎ” ሲሉ ለጠሩት ታጣቂ፣ ልዩነቶችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት፣ የክልሉ መንግሥት፥ የሀገር ሽማግሌዎችንና ከፍተኛ አመራሮችን በተደጋጋሚ በመላክ የሰላም ጥሪ ሲያቀርብ መቆየቱን አስታውቀዋል፡፡

በዋግ ኽምራ ዞን ኹለቱ ወረዳዎች፣ ትጥቃዊ እንቅስቃሴ እንደሚያደርግ ለአሜሪካ ድምፅ የተናገረውና በትክክለኛ ስሙ፣ “የአገው ሸንጎ” ሳይኾን፣ “የአገው ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ” እንደሚባል ማስተካከያ የሰጠው ተቃዋሚ አካሉ፣ የክልሉ መንግሥት የሰላም ጥሪ እንደደረሰው አረጋግጧል፡፡

የንቅናቄው የውጭ ግንኙነት ዘርፍ ሓላፊ አቶ ባየ በሬ፣ ንቅናቄው፥ ከአማራ ክልል መንግሥት ጋራ ያሉ ችግሮችን፣ በሀገር ሽማግሌዎች ሳይኾን በድርድር መፍታት እንደሚሻ አስታውቀዋል፡፡

ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

XS
SM
MD
LG