በታዋቂው ሠዓሊ እና ገጣሚ ገብረ ክርስቶስ ደስታ ስም ለተቋቋመው ቤተ መዘክር እና በውስጡ ለሚካበቱት የሥዕል ሥራዎቹ፣ በዘመናዊ አያያዝ እና አቀራረብ የተደገፈ ሰፊ የሕዝብ ተደራሽነት ዕድል እንዲመቻች ተጠየቀ፡፡
ጥያቄው የቀረበው፥ በሥነ ሥዕል፣ በሥነ ግጥም እና በመምህርነት ሞያዎች፣ የአያሌ ተጠቃሽ ሥራዎች ባለቤት የኾነውን የገብረ ክርስቶስ ደስታን ዐፅም፣ ለ42 ዓመታት ከዐረፈበት ከአሜሪካ ኦክላሃማ ግዛት ወደ ኢትዮጵያ ለማፍለስ፣ ሒደቱን የሚያስተባብር ኮሚቴ በተቋቋመበት ወቅት ነው፡፡
የጠቢቡ የሥዕል ሥራዎች፣ በአንድ ስፍራ ተሰብስበው ለተመልካች ተደራሽ እንዲደረጉ የተጠየቀ ሲኾን፣ በዐዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሥር የሚገኘውንና በሠዓሊው ስም የተቋቋመውንም ሙዝየም፣ በዘመናዊ አያያዝ እና አቀራረብ ደረጃውን የጠበቀ ይኾን ዘንድ ጥረት እንዲደረግ ጥሪ ቀርቧል።
ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።